በሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ እራሷን አጠፋች

ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አንዲት የ23 አመት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ በጋዲር ከስሩዋን በአሰሪዎቿ መኖሪያ ቤት ዉስጥ እራሷን በመስቀል ህይወቷን ማጥፋቷን የሊባኖስ ዴይሊ ስታር ገለፀ። ሳባ ማሩን በተባለዉ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ተሰቅላ ስለተገኘችዉ ኢትዮጵያ አሟሟት ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አሰሪዋ ራሚ አቡ ካሊል ለፀጥታ ሃይሎች ቃሉን እንዲሰጥ መደረጉን ከዜና ምንጩ በተጨማሪ ለማወቅ ተችሏል።