1486ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል መውሊድ ተከበረ

ጥር 26 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በዓሉ በታላቁ አንዋር መስጊድ ሲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬ ዚዳንት ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ ሙስሊሙ በተለያየ መንገድ የሙስሊሙን አንድነት ለማደፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን እንዲከላከል አሳስበዋል፡፡

ከ50 ዓመታት በላይ የቆየውን የአወልያ ተቋም በአዲስ አደረጃጀት በመለወጥ ተቋሙን ወደ ሃይማኖታዊ ዩኒቨርስቲ ለመቀየር እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታየኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአወልያ ኮሌጅ እንዲከፈት፣ የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥና መጅሊሱ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

በትናንትናው እለት በአወልያ መስጊድ ዙሪያ በቀረበው ዘገባ ላይ በአሉ በስታዲየም ይከበራል የተባለው በስህተት የቀረቡ በመሆኑ በአንዋር መስጊድ ተብሎ እንዲታረም ከታላቅ ይቅርታ ጋር እንጠይቃለን።