.የኢሳት አማርኛ ዜና

በደባርቅ ወረዳ የሚገኙ መምህራን የጀመሩት አድማ ዛሬ ማብቃቱ ተመለከተ

የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደሞዝ ጭማሪ እና የተለያዩ የመብትና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ከትናንት ጀምሮ በየትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ተቃውሞዎችን ሲያደርጉ  የነበሩት መምህራን፣ በዛሬው እለት አድማቸውን ያቋረጡት ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከወላጆችና ተማሪዎች ጋር በተደረገ ውይዒት መሰረት ነው።  የወረዳው ባለስልጣናት መምህራኑ ካደረጉት ህገወጥ የስራ ማቆም አድማ የፖለቲካ እጅ እንዳለበት ቢናገሩም፣ ይህን አይነቱን ፍረጃ የተቃወሙ አንዳንድ መምህራን ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል። ...

Read More »

መንግስት የቀድሞ ሰራዊት አባላትን እና በጡረታ የተገለሉ የኢህአዴግ ተቀናሽ ሰራዊትን ለመመለስ ውይይቶችን እያካሄደ መሆኑ ታወቀ

የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት የቀድሞ ሰራዊት አባላትን እና በጡረታ የተገለሉ የኢህአዴግ ተቀናሽ ሰራዊት አባላትን ወደ መከላከያ ለመመለስ ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች ውይይቶችን እያካሄደ መሆኑ ታወቀ በሰሜን ሸዋ ዞን 167 ተቀናሽ የሰራዊት አባላት ሰሞኑን በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ተስብስበው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የተቀናሽ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ እንዲመለሱ ከደብር ዘይት አየር ሀይል አባላት የተውጣጡ መኮንኖች ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም ፣ ...

Read More »

“የብአዴን አባል ካልሆንክ መቀደስ አትችልም ተብዬ ተባረርኩ” ሲሉ አንድ ካህን ተናገሩ

የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“የኢህአዴግ- ብአዴን አባል ካልሆንክ፤በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ መቀደስ አትችልም ተብዬ ተባረርኩ”ሲሉ አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ካህን ተናገሩ።  በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ ወረዳ ማሩ ጉቴ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ሲኖሩ የነበሩት ቀሲስ ገረመው ናደው ተሰማ፤ ለፍኖተ-ነፃነት እንደተናገሩት ከገዥው ፓርቲ በኩል የቀረበላቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ጥያቄ አልቀበልም በማለታቸው፤ከቤተ-ክርስቲያን አገልግሎታቸው ከመታገዳቸውም በላይ  በሚደርስባቸው የተለያዬ በደል  ካለፉት ...

Read More »

“በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ 130 የህሊና እስረኞች አሉ ሲሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ

የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ይህን ያሉት፤ ሰሞኑን የካቲት 3 ቀን ምሽት  በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት እነ አንዷለም አራጌን ለማስታወስ በተካሄደው የሻማ ማብራት ዝግጅት ላይ ነው።  “እነ አንዷለም ከታሰሩ ስድስት ወር ሆናቸው….” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ዶክተር ነጋሶ፤ በእርሳቸው እምነት አንዱዓለምም ሆነ ናትናኤል ንጹህ ሰዎች መሆናቸውን፤እንዲሁም የኦፌዴን ም/ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና የኦህኮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ ከኳስና ፊልም ማሳያ ቤቶች ጀርባ ወንጀሎች ተበራክተዋል ተባለ

የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እነዚህ ቤቶች የተለያዩ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችንና ፊልሞችን እንደሚያሳዩም በግልፅ በፃፏቸው የውስጥ ግርግዳ ማሳታወቂያዎቻቸው ላይ ለጥፈዋል። የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና እንደገለጠው በ 4 ኪሎ፤22፤ካሳንቺስ፤6 ኪሎና አውቶቡስ ተራ እንዲሁም ሳሪስ አካባቢዎች የሚገኙ ቤቶች የወንጀል መስሪያ ቦታዎች ሆነዋል። አንዳንዶቹ የኳስ ማሳያ ቤቶች ከበስተጀርባቸው የጫት መቃሚያና የሺሻ ማጨሻ ሆነዋል ያሉት  የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱሰትሪ ልማት ...

Read More »

ደባርቅ ከተማ የሚገኙ መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የካቲት 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደባርቅ ሚሊኒየም ትምህርት ቤትና እና የደባርቅ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህራን በዛሬው እለት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ፣ የመምህራን የመናገርና የመሰብሰብ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ጠይቀዋል። መምህራን ” የ11 በመቶው እድገት ለእኛም ይድረሰን፣ አንዱ በይ ሌላው ተመልካች የሚሆኑበት ሁኔታ ማቆም አለበት” የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የተቃውሞ ሰልፉ በነገው እለት ሊቀጥል እንደሚችል ለማወቅ ተችሎአል። በጎንደር የአንደኛ ...

Read More »

የዲንካ ነዋሪዎች ለአንድ ቀን ከቤት ባለመውጣት ተቃውሞዋቸውን ገለጡ

የካቲት 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከአርባምንጭ  65 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲካ ወረዳ ላይ አንድ ቤተክርስቲያን መቃጠሉን ኢሳት ዘግቦ ነበር። ሰሞኑን ችግሩ ተባብሶ የወረዳው ነዋሪዎች ቤተክርስቲያኑን ያቃጠሉት ሰዎች 3 የመንግስት ባለስልጣናት በመሆናቸው፣ ባለስልጣናቱ ለፍርድ ይቀረቡልን በሚል ተቃውሞ ማሰማት ጀምረዋል። መንግስት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ባለመቻሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአንድ ቀን ከቤታቸው ባለመውጣት ተቃውሞዋቸውን ገልጠዋል። በሁኔታው የተደናገጡት ከፌደራል እና ከክልል የመጡ ባለስልጣናት ...

Read More »

ዓረና ትግራይ ፓርቲ ኢህአዴግን ክፉኛ ነቀፈ

የካቲት 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርቲዉ ማእከላዊ ኮሚቴ ከጥር 26 እስከ 28/ 2004 በመቀሌ ከተማ ባደረገዉ መደበኛ ስብሰባ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አገሪቱና በተለይም የትግራይ ክልል የገጠሟቸዉን በገዢዉ ፓርቲ በመፈፀም ላይ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችን በዝርዝር ተመልክቷል። ኢህአዴግ ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበና ሀብታም የገጠር ገበሬዎች በመፈጠር ላይ እንዳለ ቢናገርም እዉነታዉ ከዚህ የተለየ፤ የህዝቡ ኑሮ እጅግ የዘቀጠና ከቀን ወደ ...

Read More »

ንግስት ሳባ የወርቅ ማዕድን የማምረቻ ስፍራ መገኘቱን የከርሰ ምድር ተመራማሪዎች ገለፁ

  የካቲት 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብሪታኒያ የከርሰ ምድር ተመራማሪዎች የንግስት ሳባ የወርቅ ማዕድን ማምረቻ የነበረዉን ስፍራ ማግኘታቸዉን የተለያዩ የእንግሊዝ ጋዜጦች ገለፁ። ከ3 ሺህ አመታት በፊት ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ወርቅ፤ የከበሩ ድንጋዮች፤ እጣን ከርቤና ቅመማ ቅመሞች ገፀ በረከት በመያዝ እስራኤልን የጎበኘችዉና ከንጉስ ሰሎሞን ቀዳማዊ ምኒልክን በመፀነስ እንደተመለሰች የምትታወቀዉ  ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ የወርቅ ማዕድን ማምረቻ ስፍራ መገኘቱን የገለፁት ዘ ጋርዲያንና፤ ...

Read More »

በደቡብ ገበሬዎች ራሳቸውን እያጠፉ አንዳንዶች ባለስልጣናትን እየገደሉ ነው

የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል ፍትሃዊ ባልሆነው የማዳበሪያ ስርጭትና እዳ አከፋፈል የተማረሩ ገበሬዎች እራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፤ አንዳንዶቹም የወረዳውን ኃላፊዎች በመግደልና ወደ አካባቢያቸው እንዳይደርሱ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ የኢህአዴግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር አውለው የሚያከፋፍሉት ማዳበሪያ የመሬቱን ሁኔታ፣ የገበሬውን ያስተራረስ ልማድ እና የገበሬውን ማሳ ይዞታ ግምት ውስጥ ሳያስገባ በግድ የሚሰራጭና የምርት ወቅት ሲደርስም ድርጅቶቹ የገበሬውን አፍንጫ ...

Read More »