ደባርቅ ከተማ የሚገኙ መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የካቲት 6 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የደባርቅ ሚሊኒየም ትምህርት ቤትና እና የደባርቅ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህራን በዛሬው እለት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ፣ የመምህራን የመናገርና የመሰብሰብ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ጠይቀዋል።

መምህራን ” የ11 በመቶው እድገት ለእኛም ይድረሰን፣ አንዱ በይ ሌላው ተመልካች የሚሆኑበት ሁኔታ ማቆም አለበት” የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የተቃውሞ ሰልፉ በነገው እለት ሊቀጥል እንደሚችል ለማወቅ ተችሎአል።

በጎንደር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ፣ በጭልጋ፣ በደቡብ ጎንደርና ትግራይ ተመሳሳይ ሰልፎች መደረጋቸውን መረጃዎች ቢደርሱንም እስካሁን ግን ለማረጋገጥ አልቻልንም።

በቅርቡ በድሬዳዋ የመምህራን ማህበር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ  ሰለማዊ ሰልፎች እንደሚደረጉ ለማወቅ ተችሎአል። ኢሳት የአማራ ክልል መምህራን የሚያነሱዋቸውን ቅሬታዎች በቅርቡ በተደጋጋሚ ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል።