የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አዲሱ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ፍሬ ተስፋ ሚካኤል ተስፋጽዮን የተባሉ ነባር የህወሀት አባል ናቸው። የሰሜን ሱዳን አምባሳደር ሆነው ከወራት በፊት የተሾሙት አባዲ ዘሙ ነባር የህወሀት አባል ሲሆኑ ፣ አሁንም ከአንድ ብሄርና ከአንድ ድርጅት የመጡ ሰው በተመሳሳይ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው መሾማቸው የመለስ መንግስት በሱዳን የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ምን ያክል ለመቆጣጠር እንደፈለገ ያሳያል ሲሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስት የአወልያን ሰላማዊ ተቃውሞ ወደ ግጭት ለመለወጥ እየጣረ ነው ተባለ
የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወሊያ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ አስተዳደር መካከል ተከስቶ ወደ ብዙሀኑ ሙስሊም የተሸጋገረውና ስምንት ሳምንታት ያስቆጠረው ተቃውሞ መፍትሔ ሳያገኝ፤ ይልቁንም ውሎ ሲያድር እየጋለና እየተጋጋመ መጥቶ እጅግ አሣሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ብዙሀኑ ሙስሊሞች ሳምንታት በዘለቀው ተቃውሟቸው የሙስሊሙን ህብረተሰብ እንዲመሩ በነሱ ምርጫ ሳይሆን በመንግስት ውክልና የተቀመጡት የመጂሊስ አመራሮች እንዲነሱላቸው እንዲሁም፤ መንግስት ፦“አህባሽ” የተሰኘውንና ከውጪ የመጣ ነው ...
Read More »የአማራ ተወላጆች ከደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ለቀው እየወጡ ነው
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ተወላጅ አርሶአደሮች ከደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ለቀው እየወጡ ነው፣ በአርሶአደሮች ላይ ዘግናኝ ደርጊትም እየተፈጸመባቸው ነው በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች ለረጅም አመታት ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ከክልሎች ነቅለው እንዲወጡ እየተገደዱ መሆኑንና በርካታ አርሶአደሮች ለዘመናት ያፈሩትን ሀብትና ጥሪት እየተነጠቁ ለስቃይ እየተደራጉ መሆኑን አንድ የመኢአድ የአመራር አካል ለኢሳት ተናግረዋል። አቶ ያሬድ ግርማ ለኢሳት እንደገለጡት በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ የአማራ ...
Read More »ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እያሳደደ ማሰሩን ቀጥሏል
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን እያጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ኢሶዴፓ/፤ከወዲሁ የማዳከምና የማፍረስ ዘመቻ እንደተከፈተበት፤ ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል። ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መድረክ ጽ/ቤት የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በአሁኑ ጊዜ የኢሶዴፓ አመራሮች በየቦታው እየታሰሩ ናቸው። መድረክ እንዳለው፤የኢሶዴፓ የዳውሮ ተጠሪ የሆኑት አቶ ታዬ ወ/ማሪያም በፈጠራ ክስ ተከሰው ሁለት ዓመት ተፈረዶባቸው ማረሚያ ቤት የገቡ ሲሆን፤ በጋሞጐፋ ዞን የከምባ ወረዳ ...
Read More »ወላይታ ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ውሀና መብራት አላገኘችም
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጡት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከ3 ወራት በፊት የጠፋው መብራት እስካሁን አልተመለሰም። የመብራት መጥፋቱን ተከትሎም የቧንቧ ውሀ አቅርቦት ተቋርጧል። ነዋሪው በውሀ ወለድ በሽታ እየተጠቃ እንደሚገኝ አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ነዋሪ ተናግረዋል። በአዲስ አበባም አንዳንድ አካባቢዎች ውሀ መቋረጡን ተከትሎ ህዝቡ በጀሪካን ውሀ ከወንዝ መቅዳት መጀመሩን ዘጋቢያችን ገልጧል። በሌላ ዜና ደግሞ በበመላ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ...
Read More »“በሀይማኖት ግጭቶች ውስጥ፤ የመንግስት እጅ አለበት” ተባለ
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ውስጥ በሀይማኖት ምክንያት በሚፈጠሩ ግጭቶች ውስጥ የመንግስት ባለሥልጣናት እጅ አለበት ሲሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ተናገሩ። ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን ያሉት፤በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና በብሮድካስት ባለሥልጣን ትብብር ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ከየካቲት 15 እስከ 17 ድረስ በተሰጠ ሥልጠና ላይ ነው። በደብረዘይት የ እንሥሳት ጥበቃ ተቋም አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው ሥልጠና ከተሳታፊዎቹ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፦”መንግስት ለምን በሀይማኖት ...
Read More »በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረሱል እያሉ ነው
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ኖርዌይ በተገኙበት ወቅት የገጠማቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሰደተኞች በጃንዋሪ 26/2012 አስገድዶ የመመለስ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በኖርዌይ መንግስታት መካከል መፈረሙ ሲቃወሙ መቆየታቸውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ አስታውሶአል። ስምምነቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያንንን በሀይል በማስገደድ ወደ አገራቸው እንደሚለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እኤአ ማርች 16 እንደሚጀመር ጠቅሶ፣ ኢትዮጵያኖችም በአለማቀፍ ደረጃ ማርች 12 በሚደረገው የተቃውሞ ...
Read More »የአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ለውጥ እንፈልጋለን አለ
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ህዝቡ በሚያስገርም ቁጣ ባለስልጣኖችን ስልጣን ልቀቁ በማለት በድፍረት ሲናገር እንደነበር ታወቀ አዲሱን የመሬት ሊዝ አዋጅ ለማወያየት በሚል ምክንያት በተጠራው ስብሰባ ህዝቡ ” እናንተ አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ባቆዩት አገር መሬት ሰጪና ነሺ ማን አደረጋችሁ፤ በሙስና የተጨማለቃችሁ መሆኑ እየታወቀ መሬት ለመሸጥ ምን የሞራል ብቃቱ አላችሁ፣ ህዝቡ ...
Read More »መቀሌ ዩኒቨርስቲ አምና ለትምህርት የላካቸው ሁሉም ከአንድ ብሄር ናቸው
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መቀሌ ዩኒቨርስቲ አምና ለትምህርት ወደ ውጭ አገር ከላካቸው 23 ሰራተኞች መካከል ሁሉም የአንድ ብሄር ተወላጆች መሆናቸው ታወቀ የፌደራል ዋና ኦዲተር ባወጣው ሪፖርት ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ዩኒቨርስቲው ከሀምሌ 2002 ዓም ጀምሮ ወደ ተለያዩ አገሮች ለስልጣና የላካቸው ሰራተኞች በሙሉ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው። ዩኒቨርስቲው አገራቀፍ ዩኒቨርስቲ ሆኖ እያለ እና ሰራተኞችም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ እና ከውጭ ...
Read More »ሱዳን ስደተኞችን አሳልፎ በመስጠት የሚፈፅመዉ ህገወጥ ተግባር ተወገዘ
የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መሰረቱን በርሊን/ ጀርመን ያደረገዉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የትብብር ኮሚቴ Solidarity Committee for Ethiopian Political Prisoners (SOCEPP) የሱዳን መንግስት በአገሩ የሚገኙ የፖለቲካ ስደተኞችን አሰገድዶ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በተጠናከረ ሁኔታ በመፈፀም ላይ ያለዉ ተግባር አለም አቀፍ ድንጋጌን የሚጥስ መሆኑን መግለፁን ኦል አፍሪካን ኒዉስ ዘገበ። የሱዳን መንግስት ፖሊሶች ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ በኡምዱርማንና በሌሎችም ከተሞች በመኖሪያ ቤቶች ...
Read More »