መቀሌ ዩኒቨርስቲ አምና ለትምህርት የላካቸው ሁሉም ከአንድ ብሄር ናቸው

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-መቀሌ ዩኒቨርስቲ አምና ለትምህርት  ወደ ውጭ አገር ከላካቸው 23 ሰራተኞች መካከል ሁሉም የአንድ ብሄር ተወላጆች መሆናቸው ታወቀ

የፌደራል ዋና ኦዲተር ባወጣው ሪፖርት ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ዩኒቨርስቲው ከሀምሌ 2002 ዓም ጀምሮ ወደ ተለያዩ አገሮች ለስልጣና የላካቸው ሰራተኞች በሙሉ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው።

ዩኒቨርስቲው አገራቀፍ ዩኒቨርስቲ ሆኖ እያለ እና ሰራተኞችም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ እና  ከውጭ አገራት የመጡ መሆኑ እየታወቀ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘውን የግማሽ ደሞዝ ህግ በመጣስ ሙሉ ደሞዝ እየከፈለ ያላከቸው 23 ሰዎች በሙሉ ከአንድ ብሄር የተውጣጡ መሆናቸው የዩኒቨርስቲውን ማንነት ያመላከተ ሆኗል።

ከ2002 ዓም በፊት ዩኒቨርስቲው ውጭ አገር ልኮ ካስተማራቸው የሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች  መካከል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸው በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያለውን የዘረኝነት አሰራር የሚያሳይ ነው።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ስር የሰደደ መሆኑንም በፌደራል ኦዲት ሪፖርት ላይ ተመልክቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide