ኢትዮጵያ አንድ ነባር የህወሀት አባል የደቡብ ሱዳን አምባሳደር አድርጋ ሾመች

የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አዲሱ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ፍሬ ተስፋ ሚካኤል ተስፋጽዮን የተባሉ ነባር የህወሀት አባል ናቸው።

የሰሜን ሱዳን አምባሳደር ሆነው ከወራት በፊት የተሾሙት አባዲ ዘሙ ነባር የህወሀት አባል ሲሆኑ ፣ አሁንም ከአንድ ብሄርና ከአንድ ድርጅት የመጡ ሰው በተመሳሳይ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው መሾማቸው የመለስ መንግስት በሱዳን የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ምን ያክል ለመቆጣጠር እንደፈለገ ያሳያል ሲሉ ዜናውን ያደረሱን አንድ የውጭ ጉዳይ ሰራተኛ ከአዲስ አበባ ገልጠዋል።

በደቡብ ሱዳን ኢምባሲ የሚሰሩት አብዛኞቹ የህወሀት አባላት በህገወጥ ንግድ መሰማራታቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የህወሀት ባለስልጣናት ቀረጥ ያልተከፈለባቸው እቃዎችን ወደ ሱዳን በማስገባት እና ከሱዳን በማስወጣት ከፍተኛ የሆነ ሀብት እያካበቱ ነው እንደ ታማኝ ምንጫችን ገለጻ።

ከሁለት አመታት በፊት በሰሜን ሱዳን የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና ወታደራዊ አታሼዎች በህገወጥ መንገድ የገቡ መጠጦችን ሲሸጡ በመገኘታቸው በካርቱም ታስረው እንደነበር ይታወቃል።

የውጭ ጉዳይ ምንጫችን እንደገለጠው በአሁኑ ሰአት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ና ም/ል ጠቅላይ ሚኒሰትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ሱዳን ይገኛሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide