የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በጣምራ እጅግ ታላቅ የሆነ ወደብና የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ላማካሄድ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ በ አፍሪካ ደረጃ ታላቅ ነው የሚባለው ፕሮጀክት 23 ቢሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት ወደ 400 ቢሊዮን የሚደርስ የኢትዮጵያ ብር ይፈጃል። ይሁንና ይህ ወጪ በማንና እንዴት እንደሚሸፈን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ፕሮጀክቱ የሚገነባውም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአድዋ ድል 116ኛው ዓመት መታሰቢያ በዓል ተከበረ
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መላው ኢትዮጵያዊ በነቂስ ወጥቶ የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ድል ያደረገበት ቀን በአዲስ አበባ ጀግኖች አርበኞች በተገኙበት ተከብሮአል። የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መላው አፍሪካን ለመቀራመት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1884 እስከ 1885 በፖርቱጋል አስታዋሽነት እና በጀርመን አዘጋጅነት የበርሊን ጉባኤ እየተባለ የሚጠራውን ስምምነት ፈርመዋል። ስምምነቱ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በሚያደርጉት ሩጫ እርስበርሳቸው እንዳይገጩ ዋስትና የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካን ህልውናም በነጮች እጅ ...
Read More »ዛሬም በጁምዓ ጸሎት ብዙ ህዝብ ተገኘ
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁምአ ( አርብ) ጸሎት እንደወትሮው ሁሉ በመቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ተገኘ ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው የጁምአ ጸሎት እስከዛሬ ከተገኘው የበለጠ ህዝብ ተገኝቶ ስነስርአቱን ተካፍሏል። በስነስርአቱ ላይ መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ ገብቶ ለመከፋፈል የሚያደርገውን ሙከራ ለማሳየት ፣ በድምጽ የተቀነባበረ ማስረጃ ለህዝብ ቀርቧል። በርካታ ሙስሊሞች መንግስት ህገመንግስቱን በመጻረር በእምነት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቱን ሲቃወሙት ተሰምተዋል።በእለቱም መጅሊስ ...
Read More »ኢትዮጵያ በህንድ ባንጋሎሬ የቆንሱላ ጽ/ቤት ከፈተች
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በህንድ ባንጋሎሬ የቆንሱላ ጽ/ቤት ከፈተች፤ የካራቱሪ ዲሬክተር የቆንሱላዉ የክብር ተጠሪ ሆነዉ ተሾሙ የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡባዊ ህንድ ካርና-ታካ ክልል ኢንቬስትሜንትን ለማስፋፋት የሚረዳ የቆንሱላ ጽ/ቤት መክፈቱን ሂንዱ ቢዝነስ የመረጃ መረብ ገለፀ። የጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከዲር የቆንሱላ ጽ/ቤቱ የተከፈተዉ አቅም በፈቀደ ተገቢዉን ቴክኖሎጂና የሰለጠነ ሃይል ለመጠቀም፤ እንዲሁም አረንጓዴዉን አብዮት ...
Read More »ሁለትን የስዊድናዊ ጋዜጠኞች ለማስፈታት የተጀመረዉ ዉይይት በመጠናቀቅ ላይ ነው
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉትን ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞችን ለማስፈታት የተጀመረዉ ዉይይት በመጠናቀቅ ላይ እንዳለ ተገለፀ የአዉሮፓ ፓርላማ አባልና የቀድሞ የቤልጅየም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊስ ሚቼል ከጠ/ሚኒስትር መለስ ጋር ያደረጉት ዉይይት ጠቃሚ እንደነበር በመግለፅ ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቤ እና ጆሃን ፔርሰን በቅርብ ቀናት ዉስጥ ከእስር እንደሚፈቱ ተናግረዋል። ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ...
Read More »ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ አረፉ
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-53 መፅሃፍትን ለህዝብ ያበረከቱት ታላቁ ደራሲ ጋዜጠኛና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ በ77 አመታቸውነው ያረፉት። ደራሲ ማሞ ከጦርነት እና ከስለላ ጋር በተያያዘ የተረጎሙዋቸው ስራዎች በብዙ አንባቢያን ዘንድ እንዲወደዱ አድርጓቸዋል። የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ የጤና ጥበቃው ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም አንጋፋው ደራሲ ማሞ ውድነህ በጠና መታመማቸውን ተከትሎ የነፃ ህክምና የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ለሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ...
Read More »ቤተ እስራኤላዊዋ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነዉ ተሾሙ
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤተ እስራኤላዊዋ በላይነሽ ዜቫዲያን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነዉ እንዲያገለግሉ መሾሙ ተገለፀ። ከ28 አመታት በፊት በቤተ እስራኤላዊነት ወደ ቅድስቷ አገር የተጓዙት የ44 አመቷ ወ/ሮ በወጣትነት እድሜያቸዉ ወደ ተለዩዋት ሃገራቸዉ በአምባሳደርነት መመለሳቸዉ የሚሰጣቸዉን ደስታ በመግለፅ የሳቸዉ ለዚህ ስልጣን መታጨት እስራኤል ለነባር ዜጎቿም ሆነ ለአዲስ ስደተኞች እኩል እድል እንደምትሰጥ ያረጋግጣል ብለዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT ...
Read More »የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ላይ የእስር ትእዛዝ ወጣባቸው
የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አብደል-ራህም መሃመድ ሁሴን በሱዳን ዳርፉር ግዛት በፈፀሙት የጦር ወንጀል እንዲጠየቁ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ ማዉጣቱን የአሜሪካን ድምፅ ዘገበ። የእስር ትእዛዙን የሰጠዉ ፍርድ ቤት ሚኒስትሩ በግድያ፤ በአስገድዶ መድፈር፤ በሰዎች ላይ አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ በማድረስና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት በደል በጠቅላላዉ በ41 ወንጀሎች እንደሚጠየቁ ገልጿል። ከዚህ ሌላ ግለሰቡ በነሃሴ 2003 ...
Read More »በመላ አገሪቱ የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ በአስፈሪ ሁኔታ እየናረ ነው
የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ፣ በድሬዳዋ፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉትን የኢሳት ምንጮች በማናገር ለማረጋገጥ እንደተቻለው የጤፍ እና የአንዳንድ የእህል ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በባህርዳር እና አካባቢዋ ለወትሮው 1 ሺ ብር ይሸጥ የነበረው ነጭ ጤፍ ዛሬ 1300 ብር ሲጨጥ ውሎአል። በድሬዳዋ ደግሞ 1ሺ ብር የነበረው ጤፍ እስከ 1250 ብር በመሸት ላይ ነው። በአዲስ አበባም እንዲሁ ...
Read More »መንግስት ባልተጠና የእርከን ስራ ህዝቡን እያማረረው ነው ተባለ
የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ፣ አማራ እና ድሬዳዋ ዘጋቢዎች እንደገለጡት መንግስት ህዝቡን ለመቆጣጠር በቀየሰው አንድ ለአምስት አደረጃጀት በመጠቀም ፣ አርሶአደሩን እና በተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎችን በግዳጅ በሳምንት ለሶስት ቀናት የእርከን ስራ እንዲሰሩ እያደረገ ነው። አርሶአደሩ እንዳሉት እርሳቸው በሚሩበት በቦረና ዞን የተለያዩ ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ታስረው መገኘታቸውን በዝርዝር ገልጠዋል አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የግብርና ባለሙያ እንደተናገሩት ከሶማሊ ክልል ...
Read More »