ዛሬም በጁምዓ ጸሎት ብዙ ህዝብ ተገኘ

የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁምአ ( አርብ) ጸሎት እንደወትሮው ሁሉ በመቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ተገኘ ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው የጁምአ ጸሎት እስከዛሬ ከተገኘው የበለጠ ህዝብ ተገኝቶ  ስነስርአቱን ተካፍሏል።

በስነስርአቱ ላይ መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ ገብቶ ለመከፋፈል የሚያደርገውን ሙከራ ለማሳየት ፣ በድምጽ  የተቀነባበረ ማስረጃ ለህዝብ ቀርቧል።

በርካታ ሙስሊሞች መንግስት ህገመንግስቱን በመጻረር በእምነት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቱን ሲቃወሙት ተሰምተዋል።በእለቱም መጅሊስ አይወክለንም የሚል ጽሁፍ የያዘ ቲሸርት ተሽጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኑር መስጊድ ምክትል ኢማም የሆኑት ሺህ ሰኢድ ፣ በቅርቡ ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጣ ንግግር በመናገራቸው መእመኑን ይቅርታ ጠይቀዋል።

ሼኩ አህባሽ የተባለውን የእስልምና አሰተምህሮ ለማስፋፋት ከመንግስት ጋር ይሰሩ እንደነበር ታውቋል። መንግስት ሙስሊሞቹ ላቀረቡት ጥያቄ የካቲት 26 መልስ እንደሚሰጥ ማስታወቁ መዘገቡ ይታወሳል።

በርካታ ሙስሊሞች ለኢሳት ጋዜጠኛ እንደገለጡት መንግስት ለጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ተቃውሞው አጠናክረው ለመቀጠል ወስነዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide