ሁለትን የስዊድናዊ ጋዜጠኞች ለማስፈታት የተጀመረዉ ዉይይት በመጠናቀቅ ላይ ነው

የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉትን ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞችን ለማስፈታት የተጀመረዉ ዉይይት በመጠናቀቅ ላይ እንዳለ ተገለፀ

የአዉሮፓ ፓርላማ አባልና የቀድሞ የቤልጅየም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊስ ሚቼል ከጠ/ሚኒስትር መለስ ጋር ያደረጉት ዉይይት ጠቃሚ እንደነበር በመግለፅ ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቤ እና ጆሃን ፔርሰን በቅርብ ቀናት ዉስጥ ከእስር እንደሚፈቱ ተናግረዋል።

 ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አዉጪ ግንባርን / ኦብነግ/ ትረዳላችሁ በማለት በሽብርተኝነት በተመሰረተባቸዉ ክስ ባለፈዉ ታህሳስ የ11 አመት እስራት የተፈረደባቸዉ መሆኑ ይታወሳል። 

በሌላ በኩል የሞቃዲሾ ሬዲዮ ጣቢያ ዲሬክተር የሆነዉ ጋዜጠኛ አቡካር ሃሰን መሃመድ ከአንድ ቀን በፊት መገደሉን  የሶማሊያ ጋዜጠኞች ብሄራዊ አንድነት ማህበር አወገዘ።

መቀመጫዉን ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ያደረገዉ የጋዜጠኞች ተንከባካቢ ድርጅት /ሲፒጄ / በሌላ በኩል በሶማሊላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር መሃመድ አብዱረህማን የተባለ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ ተገንጣዮች በክልሉ ዉስጥ ሰፍረዋል በማለት የሃሰት ዜና አቅርቧል በሚል በፖሊስ ተይዞ መታሰሩንና መደብደቡን አመልክቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide