የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ላይ የእስር ትእዛዝ ወጣባቸው

 የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አብደል-ራህም መሃመድ ሁሴን በሱዳን ዳርፉር ግዛት በፈፀሙት የጦር ወንጀል እንዲጠየቁ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ ማዉጣቱን የአሜሪካን ድምፅ ዘገበ።

የእስር ትእዛዙን የሰጠዉ ፍርድ ቤት ሚኒስትሩ በግድያ፤ በአስገድዶ መድፈር፤ በሰዎች ላይ አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ በማድረስና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት በደል በጠቅላላዉ በ41 ወንጀሎች እንደሚጠየቁ ገልጿል።

ከዚህ ሌላ ግለሰቡ በነሃሴ 2003 እና በመጋቢት 2004  በዳርፉር መንደሮች ዉስጥ የአየርና የእግረኛ ወታደራዊ ጥቃቶችን በማስተባበር ወንጀል መፈፀማቸዉን የአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህጎች አመልክተዋል። 

ፕሬዝዳንት አልበሺርን ጨምሮ 3 የሱዳን መንግሰት ባለስልጣኖች በዳርፉር በተቀሰቀሰዉና ለ300ሺህ ሰዎች ሞትና ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ከመኖሪያ ቀዬዉ ለተፈናቀለበት ግጭት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ላደረሱት የጦር ወንጀል በተጠያቂነት እንደሚፈለጉ ይታወቃል። 

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide