የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው የተደረገው የኖርዌይ መንግሥት የፖለቲካ ከለላ የጠየቁ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ከመለስ መንግስት ጋር ስምምነት መፈራራሙን በመቃወም ነው። ስምምነቱ የመኖሪያ ህጋዊ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውያን እስከ ማርች 15-2012 ድረስ አገር ለቀው ይወጣሉ። ማርች ሁለት እና 5 በኦስሎ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሥርአቱን በመቃውም አገራቸውን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ውዝግብ
የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ በነዳጅ ሀብቷ በበለፀገችው በኮርዶፋን ግዛት ዙሪያ የፈጠሩትን የይገባኛል ውዝግብ ለመፍታት፤ በኢትዮጵያ ሸምጋይነት አዲስ አበባ ውስጥ ድርድራቸውን ለመጀመር በተዘጋጁበት ጊዜ የአልበሽር መንግስት- ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት መዘጋጀቱ ተዘገበ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ልዑክ የሚዲያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ የሱዳን መንግስት ከደቡብ ሱዳን ጋር የፈጠረውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት በገለፀበት ማግስት ኬንያ፤ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ሰሞኑን ...
Read More »አንዱአለም አራጌ የመግደል ሙከራ ተደረገበት
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፈጠራ የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በአስከፊ እስርቤት ውስጥ ከሚማቅቁት መካከል የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አንዱአለም አራጌ በደረሰበት ድብደባ የተነሳ በደንብ መቆም እንደማይችልና ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታትም እንዳለበት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ የእስረኞችን የመከላከያ ማስረጃ ለማየት የተሰየመው ችሎት፣ የብይን ግልባጭ ለጠበቆቹ ባለመሰጠቱ ችሎቱን ለማስተላለፍ ተገዷል። አንዱአለም በድብደባው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የማረሚያ ...
Read More »መንግስት ለሙስሊሙ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ አልሰጠም
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወሊያ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላቀረቡት የመብት ጥያቄ መንግስት ለህዝቡ ተወካዮች፣ ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2004 ዓም መልስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ምንም እንኳ መንግስት የሰጠው መልስ በይፋ ለህዝብ ባይገለጠም መልሱ አውንታዊ አይደለም በሚል ህዝበ ሙስሊሙ እየተነጋገረበት ነው። መንግስት መጅሊሱ መጠነኛ ተሀድሶ ተደርጎለት እንዲቀጥልና የአህባሽ አስተምህሮ በመጂሊሱ የተደገፈ በመሆኑ እምነቱን የማስፋፋቱ እንቅስቃሴ መቆም የለበትም የሚል ...
Read More »ዶናልድ ፔይን በጠና ታመዋል
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ እውነተኛ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይገነባ ዘንድ ያለማሳለስ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት አፍሪካዊ አሜሪካዊው ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን፤ በጠና መታመማቸው ተዘገበ። በብዙሀን ኢትዮጵያውያን ዘንድታላቅ ስፍራ ያላቸው የኒው ጀርሲው ተወካይና የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባል ዶናልድ ፔይን የታመሙት በአንጀት ካንሰር ነው። እንደ “ፖሊቲኮ” ብሎግ ዘገባ፤ የአንጀት ካንሰሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ህመሙ በዶናልድ ፔይን ላይ ያየለባቸው ሲሆን፤ ህይወታቸው ...
Read More »ስኳርና ዘይት ተመልሰው ከገበያ ጠፉ
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች ስኳርና ዘይት ተመልሰው የውሀ ሽታ ሆነዋል፡፡ ዘጋቢያችን እንደሚለው መንግስት የዘይት ሀይቅ እንፈጥራን፣ የስኳር ተራራ እንገነባለን እያለ በመገናኛ ብዙሀን ሲናገር ቢቆይም፣ ለእቃዎች ተመን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ስኳርና ዘይት ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር ነበረባቸው። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ሸቀጦች ሙሉ በሙሉ ከገበያ በመጥፋቱ ህዝቡ እየተማረረ ነው። በሌላ በኩል የህወሀት ባለስልጣናት እና ጉናን ...
Read More »ህይወታችን ሲኦል ሆኖል ይላሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች
የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጤፍ ዋጋ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጭማሪ ማሳያቱ ህይወታችንን ሲኦል አድርጎታል ሲሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ተናገሩ ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ከሳምንት በፊት አንድ ጣሳ ጤፍ 10 ብር ሲሸጥ የነበረ ቢሆንም፣ በሳምንት ውስጥ የ8 ብር ጭማሪ በማሳየት 18 ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጤፍ ዋጋ መጨመርን ተከትሎም በርካታ እቃዎች እየጨመሩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው እንደተናገሩት በእህልና በሌሎች ...
Read More »የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ቀጠሮ ሊራዘም ይችላል
የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብርተኝነት የሀሰት ክስ ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ፣ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን በመቃወም የመከላከያ መልሶቻቸውን ለማቅረብ ለፊታችን ሰኞ የካቲት 26፣ 2004 ዓም የተቀጠሩ ቢሆንም፣ ዳኞቹ የብይኑን ዝርዝር ለጠበቆች ማስተላለፍ ሲገባቸው እስካሁን ድረስ ለማስተላለፍ ባለመቻላቸው፣ ችሎቱ ለሌላ ጊዜ ሊራዘም እንሚችል ለማወቅ ተችሎአል። ጠበቆቹ እስከ ትናንት ድረስ ብይኑ በጽሁፍ ተገልብጦ እንዳልተሰጣቸው ምንጮች ...
Read More »የደቡብ ክልል ግምገማ ሌሎች ችግሮችን ጥሎ ማለፉ ተነገረ
የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከየካቲት 19 እስከ 23 ቀን በክልሉ በተካሄደው አራተኛው ዙር አስቸኳይ ጉባኤ የአዋሳ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽብቁ መገኔ እንዲታሰሩ ሲወሰን እርሳቸውን ከጀርባ ሆነው ሲደግፉዋቸው በነበሩት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ላይ ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። ከወራት በፊት በአዋሳ ከተማ በሺ የሚቆጠሩ ቤቶች እንዲፈርሱ በተደረገበት ጊዜ ከንቲባው ከሌሎች አካባቢዎች የመጡትን ወይም መጤ እያሉ የሚጠሩዋቸውን ነዋሪዎች ቤታቸው ...
Read More »ቦሌ መንገድ የንግድ ማእከልነቱ እያከተመ ነው ተባለ
የካቲት 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በቦሌ መስመር የተጀመረው የመንገድ ግንባታ የመኪና ማቆሚያ ወይም ፓርኪንግ የሚተው ባለመሆኑ፣ የቦሌ የንግድ ማእከልነት እያበቃ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኢሳት ዘጋቢ ነዋሪዎቹን አነጋግሮ እንደዘገበው ከአብዮት አደባባይ እስከ ቦሌ አየር ማረፊያ በሚወስደው መንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አልተተወም። በዚህም የተነሳ የቦሌ የንግድ ማእከልነት የሚቀዘቅዝ በመሆኑ፣ በአካባቢው የንግድ ድርጅቶችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች እየለቀቁ ነው። በርካታ ...
Read More »