ስኳርና ዘይት ተመልሰው ከገበያ ጠፉ

የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች ስኳርና ዘይት ተመልሰው የውሀ ሽታ ሆነዋል፡፡

ዘጋቢያችን እንደሚለው መንግስት የዘይት ሀይቅ እንፈጥራን፣ የስኳር ተራራ እንገነባለን እያለ በመገናኛ ብዙሀን ሲናገር ቢቆይም፣ ለእቃዎች ተመን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ስኳርና ዘይት ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር ነበረባቸው።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ሸቀጦች ሙሉ በሙሉ ከገበያ በመጥፋቱ ህዝቡ እየተማረረ ነው።

በሌላ በኩል የህወሀት ባለስልጣናት እና ጉናን የመሳሰሉ የንግድ ድርጅቶች ስኳር አየር በአየር በመሸጥ ከፍተኛ የሆነ ገቢ እያጋበሱ ነው።

የስኳር አስመጪዎቹ፣ አከፋፋዮቹ እና ቸርቻሪዎቹ የህወሀት ባለስልጣናት እና ድርጅቶቻቸው በመሆኑ ገበያውን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ደስ ሲላቸው እጥረት እንደሚፈጥሩ ታእማኒ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘጋቢያችን ገልጧል።

ከሳምንት በፊት የጤፍ ዋጋ በአልተጠበቀ ሁኔታ ሰማይ መደርሱ የህዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሳያቆም ነው አሁን ደግሞ ስኳርና ዘይት ከገበያ የጠፉት።

ኢህአዴግ 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንዳገኘ በተደጋጋሚ ይናገራል፤ ህዝቡ ግን እድገቱን ተረት ተረት ነው ይላል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide