.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በገዳሪፍ ጥቃት ይቅርታ ጠየቀ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በገዳሪፍ አስተዳዳሪ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ይቅርታ ጠየቀ በአርማጭሆ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት የገዳሪፍ አስተዳዳሪ የሆኑት ካርም አል አባስ ከአማራ ክልል ፐሬዚዳንት አያሌው ጎበዜ ጋር ለመነጋገር ወደ አካባቢው ሲያመሩ ነው። ኢሳት በትናንት ዜናው ጥቃት የተፈጸመባቸው የካርቱም አስተዳዳሪ መሆናቸውን ቢዘግብም ፣ ሱዳን ትሪቢዩን ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ግን አስተዳዳሪው የካርቱም ሳይሆን ...

Read More »

ቤይሩት ከ60 – 80ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ተባለ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሊባኖስ ቤይሩት ከ60-80ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ተባለ፣ ከነዚህ ዉስጥ ህጋዊ የሆኑት 43ሺህ ብቻ ናቸዉ በብሪታኒያ የሚታተመዉ ጋርዲያን ጋዜጣ ይህን የገለፀዉ በቅርቡ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንሱላ ደጃፍ ላይ በአስቀጣሪዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድባ ወደ አዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ከተወሰደች በሁዋላ እራሷን ሰቅላ አጥፍታለች ስለተባለችዉ የሁለት ልጆች እናት ዓለም ደቻሳ ባወጣዉ ዘገባ ላይ ነዉ። የጋዜጣዉ ዝግጅት ክፍል በኢትዮጵያ ...

Read More »

200 የሚሆኑ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሰራተኞችን ከስራ ሊያሰናብት ነው

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ 200 የሚሆኑ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሰራተኞችን ከስራ ሊያሰናብት መሆኑ ታወቀ ቢ ፒ አር እየተባለ በሚጠራዉ የመንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የግምገማ ዉጤት መሰረት እንዲሰናበቱ የተወሰነባቸዉ ሰራተኞች በጥበቃ፤ በጥገናና በፅዳት ሙያ ለረዢም አመታት ሲያገለግሉ ከነበሩ የኤጀንሲዉ ሰራተኞች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል። ከመካከላቸዉ የ15 አመት የስራ አገልግሎት ዘመን ያሏቸዉና አብዛኛዎቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የቤተሰብ ...

Read More »

የአኝዋክ ተወላጅ የሆነ ወጣት በመከላከያ ሰራዊት ተገደለ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጊቱ የተፈጸመው ያለፈው ቅዳሜ ሲሆን ወጣቱ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በአንድ ባህላዊ ስነስርአት ላይ ተገኝቶ ስነስርአቱን በመካፈል ላይ ነበር። የጋምቤላን የጸጥታ ማስከበር ስራ ከክልሉ መንግስት የተረከቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወጣቱን በቅርቡ 19 ሰዎች ከተገደሉበት ድርጊት  ጋር እንደሚጠረጥሩት እና ለጥየቃ እንደሚፈልጉት በመግለጥ አብሮአቸው እንዲሄድ ያዙታል፤ በሁኔታው ግራ የተጋባው ወጣትም ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው እንደማይሄድ ሲገልጥላቸው አንደኛው ...

Read More »

በአርማጭሆ የካርቱም አስተዳዳሪ ጥቃት ተፈጸመባቸው

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአማራ ክልል ተቆርሶ ለሱዳን የተሰጠውን መሬት ለማስመለስ ወደ አርማጭሆ የተጓዙት የካርቱም አስተዳዳሪ ጥቃት ተፈጸመባቸው አተያር የተባለው የሱዳን ጋዜጣ እንደዘገበው የካርቱም አስተዳዳሪ የሆኑት  ከረመላ አባ ሼክ ከትናንት በስቲያ የመለስ መንግስት የለገሳቸውን መሬት በጉልበት ከአርማጭሆ ህዝብ አስመልሳለሁ በማለት ወደ አማራ ክልል እየተጓዙ ነበር። አስተዳዳሪው ወደ ቦታው ደርሰው ገበሬዎቹን ሰብስበው በማነጋገር ላይ እያሉ፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ...

Read More »

ወደ ዋልድባ ገዳም የተጓዙ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልድባን ከሚደርስበት ጥፋት እንከላከል በማለት ወደ ገዳሙ የተንቀሳቀሱ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ በርካታ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችን የጫኑ ከ5 በላይ መኪኖች መጋቢት 27  ቀን 2004ዓም ወደ ዋልድባ ገዳም ሲንቀሳቀሱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት አስቀድመው መንገድ ላይ በመጠባበቅ ምእመናኑ እንዳይንቀሳቀሴ ማገዳቸው ታውቋል። በህዝቡና በምእመኑ መካከል ውዝግብ በመፈጠሩም መነኮሳት ህዝቡን ለማግባባትና ወደ ሁዋላ እንዲመለስ ለማድረግ መቻላቸው ታውቋል። ...

Read More »

ኢትዮጵያ የተመድ ሰራተኛን በሽብርተኝነት ወንጅላ አሰረች

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ እንደዘገበው ግለሰቡ የታሰሩት ከኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ ነው። የተመድ የደህንነት ሰራተኛ የሆኑት አብዱረህማን ሼክ ሀሰን ለእስር የተዳረጉት በኦጋዴን ክልል የተጠለፉትን ሁለት የሶማሊ ተወላጆችን ለማስለቀቅ ድርድር እንዲጀመር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የመንግስት ቃል አቀባይ የሆነው ሽመልስ ከማል የተመድ ሰራተኛ ስለመታሰሩ እንደማያውቅ ተናግሯል። የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የአፍሪካ ተመራማሪ የሆኑት ...

Read More »

አቶ ሽፈራው ሺጉጤ ከቤንች ማጂ ዞን የተፈናቀሉ 800 አማሮች ብቻ ናቸው አሉ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ስፈራው ሽጉጤ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከ30 አመት በላይ የኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አሁንም ሰላማዊ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው።                                   በ2000 ዓ.ም በጉራፌርዳ ወረዳ 22 ሺ 46፣ በሜኒሻሻ 1ሺ 484 ፣ በሜኒት ጎልደያ ደግሞ 1ሺ 520 የአማራ ክልል ተወላጆች መኖራቸውን የገለጡት ፕሬዚዳንቱ ፣ የክልሉ መንግሥት በ2001 ዓ.ም አንድ ሰፋሪ ሁለት ሄክታር ...

Read More »

ባለፉት ሶስት ቀናት ከጉርፋዳ ወረዳ የተባረሩ የአማራ ተወላጆች ደብረብርሀን እና ባህርዳር ደረሱ

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች እንደገለጡት ከጉርዳፋ ወረዳ ከተባረሩት በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩት የአማራ ተወላጆች መካከል በ8 መኪኖች የተጫኑ ደብረብርሀን ላይ እንዲራገፉ ሲደርግ የተቀሩት ደግሞ ወደ ባህርዳር አምርተዋል። ከሾፌሮቹ ለመረዳት እንደተቻለው ሰዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል። ዘጋቢያችን አንዳንዶችን አነጋግሮ እንደዘገበው የሚፈናቀለው የአማራ ተወላጅ ቁጥር የመገናኛ ብዙሀን ከሚዘግቡት በእጅጉ የላቀ ነው።ተፈናቃዮቹ በአንድነት ሆነው ወደ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ስውር እስር ቤቶች ተበራክተዋል ሰዎችም በህገወጥ መንገድ እየተገደሉ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑት አንድነት ለፍትህ ና ለዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት መጋቢት 7፣ 2004 ዓም ለደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በጻፉት ድብዳቤ በዞኑ የሚገኙ በህግ ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ጠይቀዋል።   ድርጅቶቹ በሰሜን አሪ ወረዳ 67 በመቶ፣ በማሌ ወረዳ 70 በመቶ እንዲሁም በቤና ...

Read More »