በደቡብ ኦሞ ስውር እስር ቤቶች ተበራክተዋል ሰዎችም በህገወጥ መንገድ እየተገደሉ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑት አንድነት ለፍትህ ና ለዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት መጋቢት 7፣ 2004 ዓም ለደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በጻፉት ድብዳቤ በዞኑ የሚገኙ በህግ ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ጠይቀዋል።

 

ድርጅቶቹ በሰሜን አሪ ወረዳ 67 በመቶ፣ በማሌ ወረዳ 70 በመቶ እንዲሁም በቤና ጸማይ ወረዳ 15 በመቶ የሚሆኑት ስውር እስርቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በእነዚህ እስር ቤቶች በህገወጥ መንገድ ሰዎች እንደሚገደሉም ጠቅሰዋል።

በደቡብ አሪ ወረዳ በባዘት ቀበሌ ውስጥ የቀበሌው ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ማሚ ሸኮ አርሶ አድር ባዩ ወልደቡን መግደሉን እና ከቤተሰቡ በመሰወር ለመቅበር ሙከራ ማድረጋቸው በደብዳቤው ላይ ተመልክቷል።

 

ደብዳቤውን የጻፉት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ኦሞ ዞን ተወካይ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው በስውር እስር ቤቶች ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሰዎች መገደላቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ለማረጋጋጥ መቻላቸውን ገልጠው በአቶ ባዩ ወልድቡ ላይ የተፈጸመውን ድርጊትም እንደሚከተለው ያስረዳሉ

 

አቶ ስለሺ  የቀበሌው ባለስልጣናት አስከሬኑን ለመደበቅ ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበርም ይናጋራሉ

 

አቶ ስለሺ እንደሚሉት ሰሜን አሪ ውስጥ ሌላ ግለሰብም እንዲሁ በፖሊስ ተገድሎ በተመሳሳይ መንገድ ተቀብሯል

 

አቶ ስለሺ እንደገለጡት በደቡብ ኦሞ ዞን የሸንኮራ አገዳ ተክል ለማልማት የተጀመረው እንቅስቃሴ የቦዲ፣ የዲሜን፣ ባጫ እና የሙርሲ ማህበረሰቦችን የአኗኗር ባህል ሙሉ በሙሉ ያጠፋል በሚል ተቃውሞ እየገጠመው ነው

_________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide