ወደ ዋልድባ ገዳም የተጓዙ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ዋልድባን ከሚደርስበት ጥፋት እንከላከል በማለት ወደ ገዳሙ የተንቀሳቀሱ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ

በርካታ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችን የጫኑ ከ5 በላይ መኪኖች መጋቢት 27  ቀን 2004ዓም ወደ ዋልድባ ገዳም ሲንቀሳቀሱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት አስቀድመው መንገድ ላይ በመጠባበቅ ምእመናኑ እንዳይንቀሳቀሴ ማገዳቸው ታውቋል።

በህዝቡና በምእመኑ መካከል ውዝግብ በመፈጠሩም መነኮሳት ህዝቡን ለማግባባትና ወደ ሁዋላ እንዲመለስ ለማድረግ መቻላቸው ታውቋል። የወልቃይት የስኳር  ፕሮጀክት የገዳሙን ህልውና እንደሚፈታተነው ግልጽ እየሆነ ሲመጣ፣ የአካባቢው ህዝብ ቁጣ እየጨመረ መምጣቱንም ለማወቅ ተችሎአል። ተቃውሞውን የብአዴን አባላት ሳይቀሩ እየተቀላቀሉ መምጣታቸውን የሰሜን ጎንደር ተወካዮች ገልጠዋል። ህዝቡ አንድ እየሆነ ነው ብሶቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው አለው አንድ ወጣት የብአዴን አባላት ሳይቀሩ ተሳትን ለበር ማለት መጀመራቸውን አክሎአል።

የመንግስት ባለስልጣናት የህዝቡን ተቃውሞ ለማብረድ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶችን በተሌቪዥን እያቀረቡ ለማሳማን ሙከራ ቢያድርጉም አልተሳካላቸውም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ቃለምልልስ የሰጡ አንድ አባት አሁንም በፖሊስ እየታደኑ እንደሚገኙ ደጀሰላም ዘግቧል።

_________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide