ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንድ በአንድ በመዘርዝር፣ የመለስ መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች ኮሚሽን በጋምቢያ ዋና ከተማ በባንጁል ከኤፕሪል 18 እስከ ሜይ 2 ባደረገው ስብሰባ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ እስረኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በማእከላዊ እስር ቤት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ የውጭ ጋዜጠኞች ማህበር በአመቱ ውስጥ የተሻለ ስራ የሰሩ ጋዜጠኞችን ሸለመ
ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ሚያዚያ 23 በአልያንስ ፍራንሴስ ባካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ የብሉምበርጉ ጋዜጠኛ ዊሊያም ዳቪድ ሰን የኢትዮጵያ ሚዲያ ብዙ ጊዜ የሚተች ቢሆንም፣ የሚቀርቡ አንዳንድ ዘገባዎች፣ መዝናኛዎችና መረጃዎች ፣ ተስፋ የሚሰጡ ናቸው ሲሉ በስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል። በእንግሊዝኛ የፎርቹኗ ማህሌት መስፍን አሸናፊ ስትሆን ማህሌት በሰሜን ወሎ የተገኘን ማእድን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ...
Read More »በአቶ መለስ መንግስትና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤ “በሀሰት ፕሮፓገጋንዳ የመብት ጥያቄዎቻችን አይዳፈኑም” በሚል ርዕስ ባለ 15 ገጽ መግለጫ በበተነበት በትናንትናው ዕለት፤ መንግስት በፊናው የማስጠንቀቂያ እና የማስፈራሪያ መግለጫ አውጥቷል። የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ ረዥም መግለጫ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአብዛኛው የሙስሊም ህብረተሰብ ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና ተቃውሞ፤ በምርጫ 97 ወቅት ተከስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ...
Read More »ርእዮት አለሙ የ2012 የ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ፋውንዴሽን ሽልማት አሸናፊ ሆነች
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ31 አመቱዋ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ የ2012 “ካሬጅ ኢን ጆርናሊዝም ኤንድ ላይፍ ታይም አቺቭመንት አዋርድስ” ያሸነፈቸው ፣ ባሳየችው ጽናት እና ሙያውን ለማስከበር ባሳየችው ስእብና ነው። ርእዮት በአሁኑ ጊዜ በሽብርተኝነት ክስ የ14 አመት እስራት ተፈርዶባት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ትገኛለች። የመንግስት ባለስልጣናት በጓደኞቿ ላይ መስክራ ከእስር ቤት እንድትወጣ ለማግባባት ሞክረው ሳይሳካላቸው ከቀረ ...
Read More »የግል ፕሬስ አሳታሚዎች ማተሚያ ቤቶች ያቀረቡትን አዲስ ውል በመቃወም መግለጫ አወጡ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጦችና መጽሔቶችን የሚያትሙት ማተሚያ ቤቶች ለግል ጋዜጦችና መጽሔቶች አሳታሚዎች የላኩት የሕትመት ውል ቅድመ ምርመራን (Censorship) አንግሶ ሕገ መንግሥቱንና የፕሬስ ነፃነትን የሚፃረር ነው ሲሉ አሣታሚዎች ተቃውመውታል፡፡ አቤቱታቸውንም ለአቶ መለስ ዜናዊና ለአታሚዎቹ በዛሬው ዕለት አቅርበዋል፡፡ አሳታሚዎቹ የሕትመት “ስታንዳርድ” ውል ረቂቅ አዋጅ ቅጂ ከደረሳቸው በኋላ በተናጠል ሳይሆን በጋራ አቋም ለመያዝ በተደጋጋሚተሰብስበዋል፡፡ በስብሰባቸውም ላይ እንደዚህ ...
Read More »የሁለቱም ሀይማኖት ተከታዮች ከመንግስት እኩይ ሴራ እንዲታቀቡ ጥምረት አሳሰበ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጥምረት ለነጻነት፡ ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው መለስ ዜናዊ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ክብደት ስጥቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በማንቋሸሽና በማናናቅ በአለም ከሚታየው አክራሪ ሂደት ጋር በማገናኘት የምእራቡን አለም ቀልብ ለመሳብና ለዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ ሊጠቀምብትም ላይ ታች እያለ ነው። ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ሲሰራበት ...
Read More »በዋልድባ ገዳም ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ታወቀ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ገዳሙ አባት ለኢሳት እንደገለጡት ዝርፊያው የተፈጸመው ረቡእ ለሀሙስ አጥቢያ ከሌሊቱ 6 ሰአት ላይ ነው። ለመነኮሳቱ መካረሚያ ተብሎ የተሰበሰበ ከ65 ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ መዘረፉን፣ እኝሁ አባት ተናግረዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በገዳሙ አካባቢ በሚካሄደው የሸንኮራ የእርሻ ስራ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ። ከቀናት በፊት ከ20 በላይ መትረጊስ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም ለሸኚዎች ዝግ ነው
ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሺኚዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ኢሳት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ እግዱ አሁንም አለመነሳቱን ለማወቅ ተችሎአል። መንግስት ለአየር መንገድ ሰራተኞች እገዳው የተጣለው የሽብርተኝነት ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃ ስለደረሰኝ ነው ቢልም፣ አንዳንድ ወገኖች ግን የመንግስትን ምክንያት አልተቀበሉትም። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ዋነኛው ምክንያት መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ ሴት የቤት ሰራተኞችን ወደ ...
Read More »ከፌደራል መስሪያ ቤቶች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ጉድለት ተገኘ
ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ዋና ኦዲተርየፌዴራል መ/ቤቶችን የ2003 የኦዲት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ለፓርላማ ይፋ በሆነው በዚሁ ሪፖርት መሰረት በድምሩ 151 ባለበጀት መ/ቤቶች ተካተዋል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው የጥሬ ገንዘብ ሒሳብ ትክክለኛነትን፣ አያያዝና አጠባበቅን ለማረጋገጥ ባደረገው ኦዲት 1 ቢሊየን 66 ሚሊየን 524 ሺ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ሌላ በ59 መ/ቤቶች ውስጥ 1 ቢሊየን 27 ሚሊየን ብር ተሰብሳቢ ...
Read More »መከላከያ ሰራዊቱ በርካታ የጋምቤላ ነዋሪዎችን ገደለ
ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጋምቤላ ክልል በፖከዲ መንደር ውስጥ 5 ሰዎችን መግደሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከማቾቹ ውስጥ አንድ መምህር፣ ሁለት ተማሪዎችና አንድ አርሶ አደር ይገኙበታል። የአይን ምስክሮች እንዳሉት በርካታ ተማሪዎች ተኩስ በተከፈተበት ወቅት ወደ ጫካ ገብተው የሸሹ በመሆናቸው የሟቾች ቁጥር ሳይጨምር አይቀርም። በጥቃቱ የቆሰሉትም በርካታ መሆናቸው ተገልጿል። በኮጎ ወረዳ ጋሀሪ በሚባል መንደር ደግሞ ...
Read More »