በዋልድባ ገዳም ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ታወቀ

 ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ገዳሙ አባት ለኢሳት እንደገለጡት ዝርፊያው የተፈጸመው ረቡእ ለሀሙስ አጥቢያ ከሌሊቱ 6 ሰአት ላይ ነው። ለመነኮሳቱ መካረሚያ ተብሎ የተሰበሰበ ከ65 ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ መዘረፉን፣  እኝሁ አባት ተናግረዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በገዳሙ አካባቢ በሚካሄደው የሸንኮራ የእርሻ ስራ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ። ከቀናት በፊት ከ20 በላይ መትረጊስ የተደገነባቸው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር መኪኖች በሰሜን ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች  እየተዟዟሩ ህዝቡን ለማስፈራራት ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ ዋልድባ ገዳም እንዲጠበቅ፣ በኢትዮፕያ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ጠይቀዋል። በለንደን የርእሰ አድባራት ደብር ፋየን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ግርማ ንግግር አድረገዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide