ርእዮት አለሙ የ2012 የ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ፋውንዴሽን ሽልማት አሸናፊ ሆነች

ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-የ31 አመቱዋ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ የ2012 “ካሬጅ  ኢን ጆርናሊዝም ኤንድ ላይፍ ታይም አቺቭመንት አዋርድስ” ያሸነፈቸው ፣ ባሳየችው ጽናት እና ሙያውን ለማስከበር ባሳየችው ስእብና ነው።

ርእዮት በአሁኑ ጊዜ በሽብርተኝነት ክስ የ14 አመት እስራት ተፈርዶባት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ትገኛለች። የመንግስት ባለስልጣናት በጓደኞቿ ላይ መስክራ ከእስር ቤት እንድትወጣ ለማግባባት ሞክረው ሳይሳካላቸው ከቀረ በሁዋላ የቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር ሀላፊ የነበሩት ሀሰን ሽፋ ” እንዲህ አይነት አቋም ካለሽ ለምን ጫካ አትገቢም።” በማለት ተናግረዋት ነበር። በህመም በመሰቃየት ላይ ያለችው ርእዮት ፍርድ ቤት የግፍ ውሳኔ ካስተላለፈባት በሁዋላ፣ ምህረት እንድትጠይቅ ለማግባባት ሙከራ ቢደረግም እርሷ ግን አልቀበልም ብላለች። በበሳል ጽሁፎቿ ለመንግስት ከፍተኛ ራስ ምታት የሆነችው ርእዮት፣ በእስር ቤት ውስጥ በምታሳየው ጽናት ለብዙ እስረኞች አርአያ መሆኑዋም ከእስር ቤት የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሽልማቱን ከርእዮት ሌላ የፍልስጤም ብሎገርና ፍሪላንስ ጋዜጠኛ የሆነቸው አስማል አል ጋሁል እና በ አዘርባጃን የሬዲዮ ሪፖርተር የሆነቸው ከድጃ ኢስማይሎቫ አሸንፈዋል።

 ሽልማቱ ኦክቶበር 24 በሎስ አንጀልስና ኦክቶበር 29 በኒውዮርክ በሚዘጋጅ ስነስርአት ላይ ይሰጣል።

ኢሳት በርእዮት አለሙ ሽልማት የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ለመግለጽ ይወዳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide