ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ድምጾች በቴሌቪዥን የማያቀርብ ከሆነ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚተላለፈውን ስርጭት የኢትዮጵያ መንግስት ለማቋረጥ ዝግጁ መሆኑን መግለጡ ታወቀ:: የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን ያቀረበው ለአረብሳት ነው። መንግስት በመጀመሪያ በአረብ ሳት ሲተላለፍ የነበረውን ኢሳትን ፣ ቀጥሎም የኤርትራን ቴሌቪዥን ለማፈን ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ፣ ከአረብ ሳት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሥራ ተቋራጮች ለህዳሴው ግድብ ቃል ከገቡት ውስጥ የሰጡት 10 በመቶውን ብቻ በመሆኑ መንግስት አቸኳይ ስብሰባ ጠራቸው
ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስብሰባው የተገኙት ተቋራጮች ፦”መንግስት ፕሮጀክቶችን ሁሉ ለቻይና እና ለጃፓን ተቋራጮች እየሰጠ ባለበት ሁኔታ መሥራት አልቻልንም” ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሥራ ተቋራጮች ለህዳሴው ግድብ ቃል ከገቡት 150 ሚሊዮን ብር ውስጥ እስካሁን የለገሱት 10 በመቶውን ማለትም 15 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩና በማኅበር የተደራጁ 1 ሺ 400 ተቋራጮች ...
Read More »የማእከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ የዋጋ ንረቱ በ3 በመቶ ቀንሷል ይላል ህዝቡ ግን አልተቀበለውም
ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መስሪያ ቤቱ ባወጣው አዲስ መረጃ የዋጋ ንረቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነጣጠር የ3 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። የምግብ እህል ዋጋ በአንድ ወር ብቻ የ7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን መስሪያ ቤቱ ገልጧል፡፡ የመስሪያ ቤቱን ሪፖርት ህዝቡ የሚቀበለው አልሆነም። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም የእህል ዋጋ ሲጨምር እንጅ ሲቀንስ አይታይም። ጤፍ በአማራ ክልል ከ1200 እስከ 1300 ...
Read More »የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው”የተሰኘውን አዲስ አልበም ክሊፕ በይፋ ተመረቀ
ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ትናንት “ጥቁር ሰው”የተሰኘውን አዲስ አልበም ክሊፕ በይፋ ባስመረቀበት ጊዜ ፦”ዳግማዊ ምኒልክ” የሚል ተጨማሪ አዲስ ነጠላ ዜማ አሰማ። በሂልተን ሂቴል በተካሄደው በዚሁ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ ከ 700 በላይ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤መድረኩን የመራው አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ ነው። በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ፣ የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲኒግዴ ...
Read More »በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኮልፌ ቀራኒዮ ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተከሰተው ቤተክርስቲያኑዋ ለትምህርት የምትገለገልበትን ቦታ መስተዳድሩ ለመንጠቅ ሙከራ በማድረጉ ነው። ምእመናኑ የመንግስትን እርምጃ መቃወማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ አንድ ፖሊስ መሞቱም ታውቋል። ግጭቱን ተከትሎም በርካታ ምእመናን ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ፍጥጫው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ፣ ሊፈነዳ መቃረቡን ዘጋቢዎች ከስፍራው ገልጠዋል። የአካባቢው ህዝብ ስንቁን እየያዘ ወደጋዳሙ በመትመም ላይ ሲሆን፣ መንግስትም በደባርቅና አካባቢው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራዊቱን በትኖአል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው፣ በህዝቡና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ በመጨመሩ ምናልባትም ሰኔ 21 ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ...
Read More »ጎንደር ውስጥ የሁለት ሰዎች አስከሬን መሬት ላይ ተጎተተ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ፣ በሳንጃ ከተማ ሸፍተዋል ተብለው በተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሁለት ሰዎች አስከሬን ለሦስት ሰዓታት ያህል መሬት ለመሬት እንዲጎተት ተደረገ። በድርጊቱ ያዘኑና ጮኸው ያለቀሱ የከተማው ነዋሪዎች በፖሊስ ቆመጥ ተደብድበዋል። እንደ ፍኖተ ነፃነት ዘገባ፤ ሸፍተዋል ተብለው በተኩስ ልውውጥ የተገደሉት የከተማው ነዋሪዎች አቶ ሸንኮና ከፍያለው እና አቶ ዳኛቸው አያሌው ናቸው። ነዋሪዎቹ ...
Read More »50 የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸው ተነገረ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)፤ከ 50 በላይ የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ ማለቱን ቪኦኤ ዘገበ። ግንባሩ ጥቃቱን የፈፀመው፤ የ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት “ደቦች ሕሪሶ” በተባለ አካባቢ ባለፈው እሁድ ግንቦት 19 ቀን አድርሰውታል ላለው ጥቃት በወሰደው የበቀል እርምጃ ነው። ኦብነግ ባለፉት ሦስት ወራት ስድስት መኮንኖችን ጨምሮ በጠቅላላው 168 ወታደሮችን መግደሉን መግለጫው ያመለክታል። ባለፈው እሁድ ...
Read More »የደቡብ አፍሪካ ስታዲየም በተቃውሞ ድምጽ ተስተጋባ
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ያደረገውን የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመደገፍ ወደ ስታዲየም የገቡ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ መለስ መንግስትን አጠንክረው መቃወማቸው ተዘገበ። በሺዎች የሚቆጠሩ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጨዋታው ቦታ ተገኝተው ብሔራዊ ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ደቡብ አፍሪካ-ሮያል ቦፎኬንግ ስታዲየም የተመሙት አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ባንዲራቸውን እያውለበለቡ ነበር። ተቃውሞው የተጀመረው ...
Read More »በአፋር ክልል በተነሳ ግጭት ከ10 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደተናገሩት ጥቃቱን የፈጸሙት በሶማሊ ክልል በሚደገፉ የኢሳ የልዩ ሀይል አባላት ናቸው። ትናንት ከጧቱ 12 ሰአት ላይ በመደበኛ ሁኔታ የታጠቁ ልዩ ሀይሎች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት መንግስት ጥቃቱ ሲፈጸም ሊታደጋቸው አልቻለም (2፡45-03፡08)። ጥቃቱን የፈጸሙት ሀይሎች በሶማሊ ክልል እና በጂቡቲ መንግስት የሚደገፉ ልዩ የኢሳ ሀይል ታጣቂዎች መሆናቸውን የሚናገሩት ...
Read More »