.የኢሳት አማርኛ ዜና

እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ተፈረደባቸው

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ከ8 አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ አስተላለፈ በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ከተላለፈባቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል። አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የእድሜ ልክ ...

Read More »

በሲዳማ ዞን ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከሲዳማ ዞን እጣ ፈንታ እንዲሁም አጠቃላይ የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተነሳው ውጥረት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ ባለፈው ሳምንት የግንቦት7 አባላት ናቸው ተብለው የተረጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ዘጋቢያችን የገለጠ ሲሆን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት አቶ በረከትንና አቶ አባይ ጸሀየን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ፓርቲዎች በችግሩ ዙሪያ በአዋሳ ከተማ ውይይት እያደረጉ ...

Read More »

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአመራር አባሉ በጥይት ተደብድቦ የተገደለበት  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ። ”የዳኝነት ሥርዓቱም  ቅጥ ባጣ መልኩ በኢህአዴግ  አመራር የሚሽከረከር አሻንጉሊት ሆኗል” ሲልም  መኢአድ የፍትህ ስርዓቱን አጥብቆ ኮንኗል። ድርጅቱ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤  በርካታ አመራሮቹና አባላቱ   ያለምንም ጥፋታቸው በኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች  ሰብዓዊ ክብራቸው እየተገፈፈ እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ...

Read More »

የሙስሊም እንቅስቃሴ መሪዎች ታስረው ተለቀቁ

ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የደህንነት ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች አስወጋጅ ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላት የሆኑትን አህመዲን ጀበል እና ዑስታዝ አቡበከር አህመድን ለግማሽ ቀናት አስሮ ለቀቀ፡፡ የእሥሩ ምክንያት በመጪው እሁድ በአወሊያ መስኪድ ያዘጋጁትን የአንድነትና የመጅሊስ ይፍረስ ተቃውሞ ስብሰባን እንዲያቋርጡ ለማድረግ ነው ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡ ሁለቱ የኮሚቴ አባላት ለእሁድ ሕዝባዊ የጸሎትና የመጅሊስ ይፍረስ የተቃውሞ ዝግጅት የኮሚቴ ስብሰባ ...

Read More »

የምርጫ ቦርዱ አቶ ተስፋዬ መንገሻ ከሃላፊነት ተነሱ

ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የምርጫ ቦርድ ዋና ጸሐፊ በመሆን ለገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ ውለታ የዋሉት አቶ ተስፋዬ መንገሻ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ በተለይ ኢህአዴግ በ1997ቱ ምርጫ ከፍተኛ ሸንፈት ባጋጠመው የጭንቀቱ ወቅት በምርጫ ቦርዱ የተቀነባበረ ማጭበርበር በማድረግ፣በድጋሚ ምርጫዎች በቶ በመቶ የተሸነፉ ባለሥልጣናትን በአስደናቂ ሁኔታ መቶ በመቶ  እንዲያሸንፉ በማድረግ  ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ ከምርጫ 97 በኃላ ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀ ሕመም ...

Read More »

አቶ ሽመልስ ከማል ዳግም ተጋለጡ

ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ቃል አቀባይ ነኝ የሚሉት አቶ ሽመልስ ከማል ስካይፒንና ሌሎችን የኢንተርኔት የመገናኛ ዘዴዎችን የሚከለክል ህግ አላወጣንም በማለት አለም የሚያውቀውን ሀቅ ሲክዱ ቢቆዩም፣ ትናንት ቃል በሚያቀብሉለት መንግስት ተጋልጠዋል። የሕወሃት/ኢሕአዴግ ፓርላማ በትናንት ሃምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ውሎው ያፀደቀው ይህ አዲስ አዋጅ፣ ቀደም ሲል የወጣውን አፋኝ ሕግ ሙሉ ለሙሉ የሚሰርዝና፣ የድምጽና የፋክስ መልዕክትን ጨምሮ ስካይፒና ...

Read More »

ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ዙሪያ ለዓለም ባንክ ደብዳቤ ጻፈ

ሐምሌ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዓለም ባንክ፤ ኢትዮጵያ   ወደ ኬንያ የኤሌክትሪክ መስመር ለመዘርጋት  በሚል እየሰራች ላለው  የአሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ገንዘብ ከመለገሱ በፊት፤ የፕሮጀክቱ  አካባቢው እንዳማይጎዳና  የነዋሪዎች  ህይወት  እንደማይናጋ ሊያረጋግጥ ይገባል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች አሣሰበ። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች ይህን ያለው፤ ጎዳዩን አስመልክቶ  ትናንት ለዓለም ባንክ  ፕሬዚዳንት ለጂም ዮንግ ኪም በፃፈው ደብዳቤ ላይ ነው። ...

Read More »

ለአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ የተጠራው ፓርላማ የቴሌን ህግ አጸደቀ

ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-99 ነጥብ ስድስት በመቶ በአንድ ድርጅት አባላት የተሞላው ፓርላማ ለአስቸኳይ ልዩ ጉባኤ የተጠራው አዲሱንና አወዛጋቢውን የቴሌ ህግ ለማጽደቅ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ዘጋቢያችን እንዳለው በጥሪው ላይ አስቸኳይና ልዩ የተባለው ፓርላማው ካለፈው ሰኔ ሰላሳ ቀን ጀምሮ እንደተዘጋ በመቆጠሩ ነው። የፓርላማ አባላቱ ፓርላማው እንደተዘጋ የማያውቁ ሲሆን፣ የዛሬው  ልዩ ስብሰባ የተጠራው የፓርላማ አባላቱ እረፍት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ...

Read More »

አፈናው ቢጨምርም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ግን ተቃውሞአቸውን አጠናክረዋል

ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ረመዷን ፆም ከመግባቱ በፊት በአዲስ አበባ ትልቅ የ“ድምፃችን ይሰማ” የአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግና በፆም ወቅትም ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ በመጪው እሁድ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ተኩል በአወሊያ መስኪድ ቅጥር ጊቢ በሚካሄደው ህዝባዊ አንድነትና የተቃውሞ ስብሰባ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦችና ...

Read More »

የፍትህ ዋና አዘጋጅ ደኅንነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳምንታዊው ፍትህ የአማርኛ ጋዜጣና በዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የግል እንቅስቃሴ ላይ የደህንነት ኃይሎች የሁለት ቀናት የሃያ አራት ሰዓታት ግልጽ ክትትል ማድረጋቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡ በጋዜጣው የኢሜል አድራሻም ከአልሸባብ ለዋና አዘጋጁ የተላከ የሚያስመስል ቁጥር 2 የፈጠራ ደብዳቤ ከሰሞኑ ተልኳል፡፡ ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን እና እሁድ ሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጋዜጠኛ ...

Read More »