በሲዳማ ዞን ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከሲዳማ ዞን እጣ ፈንታ እንዲሁም አጠቃላይ የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተነሳው ውጥረት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ

ባለፈው ሳምንት የግንቦት7 አባላት ናቸው ተብለው የተረጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ዘጋቢያችን የገለጠ ሲሆን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት አቶ በረከትንና አቶ አባይ ጸሀየን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ፓርቲዎች በችግሩ ዙሪያ በአዋሳ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለነጻነትና ለፍትህ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደንቦባ ናቲ ለኢሳት እንደተናገሩት የሲዳማ ሽማግሌዎችና የአካባቢው ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ሲሆን ተቃውሞው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል::

አቶ ደንቦባ እንዳሉት የሲዳማ የኢህአዴግ አባላት በብዛት አባልነታቸውን እየሰረዙ ነው::

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide