ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2005 በጀት ዓመት ለአስሩ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በዓላማ ላልተገደበ ተግባር ማወሉ እያነጋገረ ነው፡፡ የአቶ ኩማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ለ2005 በጀት ያጸደቀው 16 ቢሊየን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ክፍለከተሞች እንደፈለጉት ሊመነዝሩት የሚችሉት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ባልተለመደና ከበጀት አያያዝና አጸዳደቅ ፍጹም በተለየ መልኩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በትግራይ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል
ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ ከመቀሌ በላከው ዘገባ እንዳመለከተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የክልሉ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ የአቶ መለስ ዜናዊ ህመም ነው። ሁለት አይነት አስተያየቶች ይቀርባሉ የሚለው ዘጋቢያችን፣ አንደኛው ወገን አቶ መለስ አርፈዋል ብሎ የሚያምን ሲሆን ሌላኛው ወገን ግን ህመማቸው ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ብሎ ያምናል። የአቶ መለስን ህመም ተከትሎ በክልሉ ይህ ነው የሚባል የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የጠቀሰው ...
Read More »በመንግስት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል ያለው ፍጥጫ እየጨመረ ነው
ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ ድምጻችን ይሰማ በማለት ላለፉት ተከታታይ ወራት ተቃውሞ ሲያሰሙ የቆዩ ሙስሊሞች፣ አርብ እለት የመንግስት ታጣቂዎች በአወልያ የፈጸሙትን ግድያ እና ድብደባ በመቃወም፣ እሁድ እለት ከመንግስት ፈቃድ ወጭ የሰደቃና የአንድነት ዝግጅት ማድረጋቸው መንግስትን በእጀጉ ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል። ባለፈው አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ፣ በጎጃም እና በጅማ መስመሮች ወደ አዲስ አበባ ይጓዙ የነበሩ ...
Read More »ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀረበች
ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን ዬይግባኝ አቤቱታ ተመለከተ። የመሀል ዳኛ በላቸው አንሽሶ፣ እና የግራ ዳኛው በንባብ እንደገለጡት ዛሬ መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ለውሳኔ ነበር። ዳኞቹ አሉ የተባሉ መዝገቦችን እንዲቀርቡ አዘው መመልከታቸውን ተናግረዋል። የመሀል ዳኛው ርእዮትን ለፖሊስ ቃሉዋን መስጠቱዋንና ለፍርድ ቤት ደግሞ የተከሳሽነት ቃል መስጠቱዋን የጠየቁዋት ሲሆን፣ ርእዮትም በመጨረሻው ላይ ...
Read More »ፖርላማው የውጪ አገር ሰዎች በኢንቨስትመንት ሲሰማሩ እንደ ኢትዮጽያዊያን እንዲታዩ ሰጥቶ የነበረውን ዕድል አነሳ
ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፓርላማው አስቸኳይ ጉባኤ ከአገሪቱ የ2005 በጀት ጋር ተያይዞ የጸደቀው የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ ከዚህ በፊት በትውልድ ኢትዮጽያዊያን ያልሆኑ የውጪ አገር ሰዎች በኢንቨስትመንት ሲሰማሩ እንደ ኢትዮጽያዊያን እንዲታዩ ሰጥቶ የነበረውን ዕድል አነሳ፡፡ አሁን በሥራ ላይ ባለው የኢንቨስትመንት አዋጅ አንቀጽ 37 መሰረት የውጪ ዜጎች አስቀድሞ የጸና የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ...
Read More »ከነገ በስቲያ በኒውዮርክ ታላቅ ሰልፍ ይደረጋል
ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነ አቶ አንዷለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ በቅርቡ የተላለፈውን ፍርደ-ገምድል ውሳኔ እና የዚያኑ ዕለት ወደ አወሊያ በመግባት በሙስሊም ወገኖች ላይ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጭፍጨፋ በመቃወም ከነገ በስቲያ በኒው ዮርክ ታላቅ ሰልፍ እንደሚደረግ ታወቀ። የሰልፉ አስተባባቲዎች እንደገለጹት ፤እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 19 ቀን ከ 12 ፒ.ኤም እስከ 2 ፒ.ኤም በኒው ዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ...
Read More »መንግስት አቶ መለስ ዜናዊ መታመማቸውን አመነ
ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብሉምበርጉ ዊሊያም ዳቪድሰን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው አቶ መለስ የአፍሪካን ህብረት እና ሌሎች ስብሰባዎችን መሳተፍ ያልቻሉት በህመም ምክንያት ነው። “ለህይወት በሚያሰጋ በሽታ አልታመሙም፣ እንደማንኛውም ሰው ህክምና ማግኘት አለባቸው፣ ህክምናቸውን ጨርሰውም በቅርቡ ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ ” በማለት አቶ ሀይለማርያም ተናግረዋል። ከሳምንት በፊት የመንግስት ቃል ...
Read More »በዳባት ከተማ አንድ ነዋሪ የቀበሌውን ባለስልጣን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ሰዎችን ገደለ
ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ቀበሌ 03 ነዋሪ የነበረ አንድ ግለሰብ የቀበሌው ሊቀመንበር የሚያደርስበትን ጫና ለመቋቋም ባለመቻሉ ሊቀመንበሩን፣ ባለቤቱን እና ሌላ አንድ የሊቀመንበሩ አጋር የሆነ ሰው ገድሎ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ክፉኛ አቁስሎአል። በፍትህ እጦት የተማረረው ግለሰብ ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ እጁን ለመንግስት የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ እንደፈለጋችሁ አድርጉኝ የልቤን አድርሻለሁ በማለት መናገሩን ዘጋቢዎቻችን ...
Read More »የአውሮፓ ህበረት በእነ አቶ አንዱለአም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዘ
ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ መሪዎችን አወዛጋቢ በሆነው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ሰበብ አድርጎ ማሰሩ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር እንዲተች አድርጎታል። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ካተሪና አሽተን የፍርድ ሂደቱን አዲስ አበባ በሚገኙ ዲፕሎማቶች አማካኝነት ሲከታተሉት መቆየታቸውን ያወሳው የህብረቱ መግለጫ፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ራሱዋን ከሽብረተኝነት የመከላከል መብት ቢኖራትም ፣ ...
Read More »በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን የሃይል እርምጃ” ተቃወሙ
ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “መንግስት በአዋልያና በአንዋር መስጊድ ተሰባስበው በሰላማዊ መንገድ ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ባቀረቡ ነዋሪዎች ላይ የወሰደውን የሃይል እርምጃ” ተቃወሙ። ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን በግል ተነሳስተው በቆንስሉ ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተሰባስበው “በንጹሃን ምዕመናን ላይ የተወሰደው እርምጃ አግባብነት እንደሌለው ለማሳዎቅ፤ የታሰሩት እንዲፈቱ፤ የሞቱት ሙሉ መረጃ እንዲሰጣቸውና መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ...
Read More »