በዳባት ከተማ አንድ ነዋሪ የቀበሌውን ባለስልጣን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ሰዎችን ገደለ

ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ቀበሌ 03 ነዋሪ የነበረ አንድ ግለሰብ የቀበሌው ሊቀመንበር የሚያደርስበትን ጫና ለመቋቋም ባለመቻሉ ሊቀመንበሩን፣ ባለቤቱን እና ሌላ አንድ የሊቀመንበሩ አጋር የሆነ ሰው ገድሎ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ክፉኛ አቁስሎአል።

በፍትህ እጦት የተማረረው ግለሰብ ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ እጁን ለመንግስት የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ እንደፈለጋችሁ አድርጉኝ የልቤን አድርሻለሁ በማለት መናገሩን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል።

ግለሰቡ ከሊቀመንበሩ ጋር ያለውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት ጥረት ያደርግ ነበር ተብሎአል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide