የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በግምገማ ላይ መሆናቸውን ተሰማ። ይህንንም ግምገማ ተከትሎ ግምገማዎቹ በሚካሄድባቸው ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት አባላት፤ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን የመጣው ዜና ያብራራል።ከሻለቃ ማዕረግ ጀምሮ እስከ ጀነራል ማዕረግ ድረስ ለሚገኙት ለኢትዮጲያ የመከላከያ ሠራዊት አበላት የተዘጋጀው ግምገማ፤ እስከመቼ እንደሚቀጥል የታወቀ ነገር የለም። በግምገማው ማጠቃለያ ለሠራዊቱ አባላት የጠ፨ሚር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የማዳበሪያ አምራቹ ያራ ለባለስልጣናት ጉቦ ይሰጣል ተባለ
(Aug. 15) በኖርዌይ የሚታተመውና ከፍተኛ ተነባቢነት ካላቸው ጋዜጦች አንዱ የሆነው አፍተንፓስት የተሰኘው ጋዜጣ በቅርቡ ባወጣው የምርመራ ዘገባ፤ ያራ በመባል የሚታወቀው የማዳበሪያ አምራች ኩባንያ ለኢትዮጲያ መንግስት ከትርፍ 30 ፐርሰንት ለማካፈል መዋዋሉን አጋለጠ። ሂውማን ራይትስ-ዎች ማዳበሪያን ገዢው ፓርቲ እንደ ስልጣን ማስፈጸሚያ መሳሪያ እንደሚጠቀምበት አጋልጦ እንደነበር ያተተው ይኸው ጋዜጣ፤ በቅርቡ ኢትዮፓስት በሚባል የማዳበሪያ ኩባንያ ስም የተፈጸመው ስምምነት አምባገነናዊውን ስርአት እንደማጠናከር ይቆጠራል ሲል አፍተን ...
Read More »አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል
(Aug. 15) አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ሆስፒታል መግባታቸውን በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዜናዎችን በቅርበት በመዘገብ የሚታወቀው ደጀ ሰላም ድረ-ገጽ ዘገበ። ከፓርያሪክ ረዳቶች አንዱ የሆኑትን አባ እንቁ ባህርይ ግን፤ “የለም አልታመሙም እሳቸው ቤት ነው ያሉት” ብለዋል። አባ ጳውሎስ ትናንት ምሽት በጠና ታመው ባፋጣኝ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል እንደተወሰዱ የሚያትተው ይኸው ዜና ዘገባ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን ችለው መራመድ አቅቷቸው መኪናቸው ...
Read More »ሂውመን ራይትስ ወች በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰውን በደል አወገዘ
(Aug. 15) የኢትዮጵያ መንግስት አፍሶ ያሰራቸውን 17 የሙስሊም መሀበረሰብ መሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ። የታሰሩ ሙስሊሞች ላይ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ መፈጸሙን አወገዘ። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሲካሄድ በነበረው የሙስሊሙ ማሀበረሰብ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ሲያስተባብሩ የነበሩ እኒህ 17 መሪዎች ጠበቃ የማናገር መብታቸው ታግዶ ከሶስት ሳምንታት በላይ መታሰራቸው ኢፍትሀዊ መሆኑን ሂውማን ራይት ዎች በመግለጫው አስታውቋል። ከጁላይ 13 ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ...
Read More »በአዋሳ ጨምበላላ በዓል ላይ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰማ
(Aug. 15) በአዋሳ ከተማ፤ ፊቼ ጫምባላላ በመባል የሚታወቀውን የሲዳማ ብሄረሰብ አዲስ አመት ለማክበር የወጡ፤ ከአምስ መቶ ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን መንግስትን የተቃወመ ትእይንት አደረጉ። በትላንትናው እለት በተጀመረው በዚህ በአል ላይ ህዝቡ ከዚህ ቀደም የተነሳውን የሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄ ዳግም አስተጋብቷል። ኢህአዴግንና የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ችፈራው ሽጉጤንም በጽኑ አውግዟል። ህዝቡ በጭፈራው መሀል ፍትህና ነጸነት በመጠየቅ፤ ይህን የነፈገውን የኢህአዴግ መንግስት፤ “ኢህአዴግ ሰለቸን፤ በቃችሁን፤” ...
Read More »የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ፤ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀረበ
(Aug. 15) የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለን በ3 የተለያዩ ክሶች ተከሶ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ። ተመስገን ደሳለኝ የክስ መጥሪያ ሳይደርሰው መከሰሱን የሰማው በሬድዮ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የገለጸ ሲሆን፤ ይህም የደርግ ግዜውን አፈሳና እስራት አስታውሶኛል ብሏል። በከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረበው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ “ችሎት አልተሟላም ተብሎ” ክሱ ሀሙስ ነሃሴ 17 ቀን እንዲታይ ቀጠሮ ...
Read More »ሲ ኤን ኤን በመለስ ዜናዊ መሰወር ፍርሀት መንገሱን ዘገበ
(Aug. 15) የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መሰወር የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል። ሲ ኤን ኤን ዘወትር ከመድረክ የማይጠፉት አቶ መለስ ዜናዊ፤ ከሁለት ወራት በላይ የት እንዳሉ አይታወቅም ሲል ዘግቧል። መንግስት በሚያሰራጨው የተቆጠበ መረጃ መላምቶች እየሰፉ መቀጠላቸውን፤ በሀገሪቱ ፍርሀት መንገሱንም ሲ ኤን ኤን ዘርዝሯል። “ስለ ጠ/ሚ/ሩ ሁኔታ ለማውራት ፍርሀት አለ። ይህ በሕግ ሳይሆን በሀይል የሚመራ ሀገር ነው።” በማለት ለሲ ኤን ...
Read More »አቶ ስብሐት ነጋ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ መመለስ መናገራቸው ስህተት እንደነበረ ለኢሳት ገለጡ
ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንት በፊት ያስታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ አባባላቸው ስህተት መሆኑን ለኢሳት ገለጡ። አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ አመት በፊት አቶ መለስ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የማረጋገጥም ሆነ የማስተባበል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል። አንጋፋው የህወሀት ታጋይ አቶ ስብሀት ነጋ ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው ...
Read More »አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨመረ
ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግብርና ሚኒስቴር እና የውጭ ለጋሾች ትናንት በጋራ ያቀረቡት ሰነድ እንደሚያሳየው ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን 200 ሺ ወደ 3 ሚሊዮን 700 ሺ ከፍ ብሎአል። ለእነዚህ ተረጅዎች ከ189 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ3 ቢሊዮን 4 መቶ ሚሊዮን በላይ ብር እንደሚያስፈልግ ታውቛል። 41 በመቶ የሚሆኑት ተረጅዎች ...
Read More »የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በግብጹ ባለስልጣን ንግግር ቅሬታውን ገለጸ
ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ዞር ሲሉ፤ ግብፆች ፦” ኢትዮጵያውያን ከጥቅማቸው በተቃራኒ ይቆማሉ” ብለው ማሰባቸው ስህተት ነው” ሲሉ አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ፡፡ በኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ያሉት፤ አንድ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ሳምንት ፦” ከመለስ ዜናዊ በሁዋላ የሚኖረው አዲሱ የኢትኦጵያ አመራር -ከአዲሶቹ ...
Read More »