መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በግምገማ ላይ ናቸው

የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በግምገማ ላይ መሆናቸውን ተሰማ። ይህንንም ግምገማ ተከትሎ ግምገማዎቹ በሚካሄድባቸው ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት አባላት፤ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን የመጣው ዜና ያብራራል።ከሻለቃ ማዕረግ ጀምሮ እስከ ጀነራል ማዕረግ ድረስ ለሚገኙት ለኢትዮጲያ የመከላከያ ሠራዊት አበላት የተዘጋጀው ግምገማ፤ እስከመቼ እንደሚቀጥል የታወቀ ነገር የለም።

በግምገማው ማጠቃለያ ለሠራዊቱ አባላት የጠ፨ሚር መለስ ዜናዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጣቸው እየተጠበቀ ነው። ይህ ግምገማ እንደተጠናቀቀ በየደረጃው  ሌላ ግምገማ እንደሚቀጥል የኢሳት ምንጮች አብራርተዋል።