.የኢሳት አማርኛ ዜና

የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኮሎኔል ጉዕሽ ከባቢሌ ወደ ሃረር ሲጓዙ ዳካታ በሚባል ቦታ ላይ ሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓም ባልታወቁ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል። አዛዡ ወደ ባቢሌ ብቻቸውን ተጉዘው እንደነበር የሚገለጹት ምንጮች፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ከመኪናቸው አውርደው ገድለዋቸዋል። አስከሬናቸው ሃምሌ 29 ቀን 2010 በምስራቅ እዝ አባላት ...

Read More »

የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የጌዲዮ ብሄረሰብ አባላትን ወደ ቦታቸው ለመመለስ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የጌዲዮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሃይለማርያም ተስፋዬ ህዝቡን ያነጋገሩ ቢሆንም፣ ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ህዝቡ ተቃውሞውን በሰልፍ ገልጿል። ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው ከመመለሳቸው በፊት የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው፣ ለወደመባቸው ንብረትም አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸው ...

Read More »

በኮምቦልቻ የባቡር ሃዲድ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

በኮምቦልቻ የባቡር ሃዲድ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ያፒ መርከዚ በተባለ የቱርክ ኩባንያ ከ አዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ በሚሰራው የባቡር መንገድ ዝርጋታ ስራ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ትናንት ወደ አደባባይ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ ከደቡብ ወሎ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ከኩባንያው መሪዎች ጋር ለመነጋጋር ቀጠሮ የያዙ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ለጥያቄያቸው ...

Read More »

በመስቀል ዓደባባይ የቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ቀጠሮው ተራዘመ

በመስቀል ዓደባባይ የቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ቀጠሮው ተራዘመ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገቡት የለውጥ ጅምሮችን በመደገፍ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም የምስጋና እና የድጋፍ ሰልፍ ላይ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል። በወቅቱ የደረሰውን ጥቃት አቀናብረዋል፣ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ...

Read More »

በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

በጅግጅጋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ ከትናንት ጀምሮ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ቤቶቻቸው የተዘረፉባቸው እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት የወደሙባቸው ዜጎች በብስጭት ተቃውሞ ለማድረግ ቢያስቡም፣ የአገር ሽማግሌዎች በቀልን በበቀል መመለስ ትክክል አይደለም በማለት እንዳረጋጉዋቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ከስልጣን የተነሱ ሲሆን ፣ በዛሬው እለት በቁጥጥር ...

Read More »

በተርጫ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው።

በተርጫ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ በመከለከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብነት ቢበርድም ፣ ዛሬም ከፍተኛ ውጥረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በከተማው ለደረሰው ጥፋት ባለስልጣናቱን ተጠያቄ የደርጋሉ። ችግሩ እንዴት እንደተነሳ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑትን መመህር ፍሰሃ ተስፋዬን አነጋግረናቸዋል።

Read More »

“ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ጠላትነት ተግባር ነው” ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

“ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በየትኛውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሕዝብ ጠላትነት ተግባር ነው” ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በከፈሉት መራር መስዋዕትነት ባለፉት አራት ወራት አገራዊ አንድነት እና መግባባት፤ እንዲሁም የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በአንፃራዊነት መከበራቸውን፤ ...

Read More »

ኦነግ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረመ

(ኢሳት ዲሲ—ነሃሴ 1/2010)  የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ። ኦነግ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ለመቀጠል መስማማቱም ተመልክቷል። ከኦሮሞ ነጻነትግንባር ጋር የሰላም ሥምምነት ለመፈራረም ወደ አስመራ ያቀኑት የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን  ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውም ታውቋል። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪዎች ጋር የሰላም ሥምምነት ለመፈራረም ትናንት ወደ ኤርትራ የተጓዙት  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ...

Read More »

ጂጂጋ በመረጋጋት ላይ ናት ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 1/2010)ጂጂጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን በማረጋጋት ላይ መሆኑ ተገለጸ። ላለፉት ሶስት ቀናት በቀውስ ውስጥ የቆየችው ጂጂጋ በአንጻራዊ ሁኔታ መረጋጋት እንደሚታይባት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ኢሳት ያነጋገራቸውና በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋ። መከላከያ ሰራዊቱ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን መጠነኛ ለውጥ እያየን ነው ብለዋል። በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች አሁንም ተደብቀው ያሉ ነዋሪዎች ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። በድሬዳዋም ዛሬ ...

Read More »

ሶማሌ ክልል የልዩ ፖሊስ አመራር አባላት ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 1/2010) የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አብዲ ኢሌ ቁልፍ የልዩ ፖሊስ አመራር  አባላት መታሰራቸው ተገለጸ። ከክልሉ ፕሬዝዳንትነታቸው ተነስተው በሌላ ሰው የተተኩት አብዲ ኢሌ  የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። በኋላ ላይ ግን አብዲ ኢሌ በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ጅጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት ወደ አዲስ አበባ እንደተወሰዱ ዘገባዎች አመልክተዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂጂጋ ...

Read More »