Author Archives: Central

በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ

ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ አድርገዋል።   የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ካስደረጉ በሁዋላ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል ሆና መመረጡዋ ተተቸ

ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰሞኑን ባካሄደው ምርጫ አስከፊ ሰብአዊ መብቶችን ጥሰት የሚፈጽሙ በርካታ አገሮችን መምረጡ በሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል። የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅቶች እንዳሉት ሰኞ እለት ከተመረጡት 18 አገሮች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አገሮች ሶስት ብቻ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ለአፍሪካ 5 መቀመጫዎችን የሰጠ ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ኬንያና ሴራሊዮን ለቦታው ተመርጠዋል። ...

Read More »

የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 15 ነጥብ 8 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተነገረ

ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማእከላዊ ስታትስቲክስ እጀንሲ እንዳለው ያሳለፍነው ወር የዋጋ ግሽበት ከመስከረም ወር ጋር ሲነጻጸር 0 ነጥብ 7 ቀንሷል። ለዋጋ ግሽበቱ መቀነስ የምግብ ሸቀጦች መቀነስ አስተዋጽኦ አድርጓል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ወራት የቀነሰ ሲሆን ፥ መስክረም ወር ላይ 17 ነጥብ 6 በመቶ የነበረው የምግብ ዋጋ  በጥቅምት ወር ወደ 13 ነጥብ 2 በመቶ መውረዱ ተገልጿል። ...

Read More »

የሙስሊሙ ንቅናቄ ከሀገሪቱ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን መረጋጋት የሚያሰጋ ነው ተባለ

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ መንግስት የእስልምና ምክር ቤቱንና የእምነቱን ስርአት ለመቆጣጠር የሚያደርገው ተግባር ከሀገሪቱ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን መረጋጋት የሚያደፈርስ መሆኑ ተገለጠ:: የአመሪካ መንግስት ሪፖርት የሀገሪቱ የእስልምና ምክር ቤት አመራር አባላት ምርጫ ተካሂዶ አመራሩ ቢሰየሙም የሙስሊሙ ህዝብ ተቃውሞ መቀጠሉን አስታውቆ መንግስት ተቃውሞውን በሀይል ለመቆጣጠር መሞከሩን አውግዞል:: የኢትዮፕያ መንግስት የሙስሊሙን ህብረተሰብ ፣ አመራርንና ተቃውሞውን በሀይል ለመቆጣጠር ...

Read More »

በላፍቶ የተፈናቀሉት አባወራዎች 30 000 ደረሱ

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 01 ቤታቸው የፈረሰባቸውና ለጎዳና የተዳረጉ አባወራዎች ቁጥር 30 000 መድረሱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገለጡ። ወደጠቅላይ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ ጽፈት ቤት ተሰብስበው በመሄድ ጥያቄዎቻቸውን ለማቅረብ መሞከራቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ያገኙት መልስ በፖሊስ መደብደብና መታሰር መሆኑን ለኢሳት ሬዲዮ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ህገወጥ ናቸው ሲል ባለፈው ሳምንት ማፍረስ ከጀመራቸው ...

Read More »

የአቡነ ናትናኤልን ጥረት የሚያሰናክሉ ወገኖች መነሳታቸው

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ዕርቅን ለማውረድ የሚደረገው ጥረት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት የአቡነ ናትናኤልን ጥረት የሚያሰናክሉ ወገኖች መነሳታቸው ተሰምቷል። በዚህም የተነሳ አቡነ ናትናኤል በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ሐገረ ሥብከታቸው መሄዳቸውን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት አጥብቀው ይሻሉ የሚባሉት ዓቃቢ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ወደ ሠላም በሚወስደው መንገድ ላይ የሚያደርጉት ጥረት በአንዳንዶች ...

Read More »

እስክንድር ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታዋቂው ጋዜጠኛ አስክንድር ነጋ መኖሪያ ቤት እና የወላጅ እናቱ መኖሪያ ቤት ለመውረስ በነገው እለት እስክንድር ፍርድ ቤት መጠራቱ ታወቀ። እስክንድር በጉዳዩ ላይ አልከራከርም ማለቱ የተሰማ ሲሆን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልም ድርሻዋን ላለመጠየቅ መወሰኗን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስርዳ። በአሸባሪነት ክስ ተመስርቶበት የ18 አመት እስራት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ወህኒ ቤት ከገባ አንድ አመት ...

Read More »

ኢህአዴግ የቤት ልማት ፕሮግራሙን ከምርጫው ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ ነው

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-40 በ60 እየተባለ የሚታወቀውና በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ከአዲስአበባ እና አካባቢ ምርጫ ጎን ለጎን ለማከናወን ኢህአዴግ ዕቅድ መያዙን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ በአቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚመራው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነትና አመራር ሰጪነት በተለይ በአዲስ አበባ ለመጀመር የታቀደው ይህው ፕሮጀክት ከምርጫው ጎን ለጎን ለማስኬድ የተፈለገው ሕዝቡ ኢህአዴግ ለልማት የሚያደርገውን ጥረት ተረድቶ ልማቱን ለማስቀጠል ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ ...

Read More »

‹ ጋዜጠኛ እስክንድር የ 7 ዓመት ታዳጊ ህፃን ልጁን ናፍቆት እስክንድርን፦

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነገ ማክሰኞ ህዳር 4 ቀን 2005 ዓ.ም  በጋዜጠኛ  እስክንድር ነጋ ንብረት ዙሪያ ውሳኔ ለማሳለፍ  የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የሚሰየም ሲሆን፤ቃሊቲ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር   እዚያው እስር ቤት ትናንት የሁለት ቤት ካርታዎች የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል።   ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ማስታወሻ ከሆነ፤ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ሁለት ቤቶች አንዱ በእናቱ ...

Read More »

በጅጅጋ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ህዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፣ ሰራተኞችና ጎብኝዎች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የሶማሊ ክልል ዋና ከተማ በሆነው ጅጅጋም ሆነ ከጅጅጋ ከተማ ራቅ ባሉ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተወላጅ የኦጋዴንና የሌሎችም ጎሳዎች አባላት እንዲሁም በክልሉ ውስጥ በሚኖሩ የሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የመንግስት ሰራተኛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመሄድ በአካባቢው ይሰሩ ...

Read More »