እስክንድር ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የታዋቂው ጋዜጠኛ አስክንድር ነጋ መኖሪያ ቤት እና የወላጅ እናቱ መኖሪያ ቤት ለመውረስ በነገው እለት እስክንድር ፍርድ ቤት መጠራቱ ታወቀ።

እስክንድር በጉዳዩ ላይ አልከራከርም ማለቱ የተሰማ ሲሆን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልም ድርሻዋን ላለመጠየቅ መወሰኗን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስርዳ። በአሸባሪነት ክስ ተመስርቶበት የ18 አመት እስራት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ወህኒ ቤት ከገባ አንድ አመት አልፍታል፤በነጸው ፕሬስ ውስጥ ባለው ተሳትፎ በኢሀአዴግ ዘመነ መንግስት ለ9ኛ ግዜ የታሰረ እስክንድር ነጋ በሳመንቱ መጨረሻ ወሂኒ ቤት ሊጠይቀው ለሄደው የ6 አመት ልጁ ናፍቆት እስክንድር ስራዕቱ ሲለወጥ ቤትህን ታግኝዋለህ ሲል በፖሊሶች ፊት ሲናገር ተደመጣል። ከጋዜጠኛ እስክንድር በተጨማሪ የወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ንብረትም እንዲወረስ የተወሰነ ሲሆን የነገው ቀጠሮ አንዱአለምን ስለመጨመሩ የታወቀ ነገር የለም።