የሙስሊሙ ንቅናቄ ከሀገሪቱ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን መረጋጋት የሚያሰጋ ነው ተባለ

ህዳር 4 (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ መንግስት የእስልምና ምክር ቤቱንና የእምነቱን ስርአት ለመቆጣጠር የሚያደርገው ተግባር ከሀገሪቱ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን መረጋጋት የሚያደፈርስ መሆኑ ተገለጠ::

የአመሪካ መንግስት ሪፖርት የሀገሪቱ የእስልምና ምክር ቤት አመራር አባላት ምርጫ ተካሂዶ አመራሩ ቢሰየሙም የሙስሊሙ ህዝብ ተቃውሞ መቀጠሉን አስታውቆ መንግስት ተቃውሞውን በሀይል ለመቆጣጠር መሞከሩን አውግዞል::

የኢትዮፕያ መንግስት የሙስሊሙን ህብረተሰብ ፣ አመራርንና ተቃውሞውን በሀይል ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት በሀገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት ከማባባሱ አልፎ የአፍትሪካ ቀንድ አካባቢ ችግር ውስጥ የሚከት ነው ብሎል።

የአለም አቀፉ ሀይማኖታዊ ነጻነት የዩኤስ ኮሚሽን ባሰራጨው ሪፖርትም የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ የሆኑ ሙስሊሞችን አስሮ 29ን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሞክረዋል ብሎ መክሰሱን ያተተ ሲሆን መንግስት ሙስሊሙንና አመራሩን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት ችግር እየገጠመው መሆኑን ያሳያል ብሎል።

የኮምሽኑ ሊቀመንበር ካትሪና ላንቶስ የዩናይትድ ስቴት መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባው መንግስት ጋር እንዲነጋገር ጥሪ በማድረግ ሀይማኖታዊ ማህበረሰብን በአሸባሪነት ስም የማፈንና የማሰሩ እርምጃ ለበለጠ አክራሪነት ፣ ለከፋ አለመረጋጋትና ብጥብጥ የሚዳርግ ነውው ብሎል።