መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከነገ በስቲያ ማርች 20፣ 2013 በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ት ቤት ፊት ለፊት ኢህአዴግ በእመነት ተቋማት ላይ እአካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ ሙስሊም ወገኖች ያቀረቡትን የእመነት ነጻነት ጥያቄ ወደ ጎን መግፋቱን በመቃወም እና የሚካሄድባቸውን አፈናና ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹህን ዜጎች ላይ የሚካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም፣ በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ...
Read More »Author Archives: Central
አልሸባብ የኢትዮጵያ ጦር የያዘውን ከተማ መልሶ ያዘ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ እና ከሶማሊያ መንግስት ወታደሮች ከፍተኛ ጥቃት ሲደርስበት የቆየው አልሸባብ፣ ትክክለኛ ምክንያቱ ባልተወቀ ሁኔታ የኢትዮጵያ ጦር ከባይደዋ አቅራቢያ የምትገኘዋን የሁድሩ ከተማን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ፣ ከተማዋን መልሶ ተቆጣጥሯል። የከተማዋ ነዋሪዎች አልሸባብ አካባቢውን ለረጅም ጊዜ ከቦ መቀመጡ የምግብ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን በምሬት ሲናገሩ መደመጣቸውን ጋሮየ ኦን ላይ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ከተማዋን ለቆ ስለወጣበት ...
Read More »መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ” በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን ...
Read More »በኮብል ስቶን ሰራተኞች ጠብ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ ቦሌ ለሚ በሚባል አካባቢ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ኮብልስቶን በሚሰሩ ሰዎችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ፍኖተ ነጻነት ዘገበ፡፡ የግጭቱ መንስኤ የሞባይል መጥፋት እንደሆነ እና በዚህም ኮብልስቶን ትሰራ የነበረችን የአንዲት የአካባቢው ነዋሪ ሴት ጡት ሌላው ሰራተኛ ...
Read More »አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በአስገድዶ መድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት ተዘገበ። ሠራዊት በበኩሉ <<ወሬው በሬ ወለደ >>ነው ይላል።
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገዥው ፓርቲ ቀንደኛ ደጋፊነቱ የሚታወቀው አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በ አስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል ክስ እንደቀረበበት አዲስ አድማስ ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሆነው ሠራዊት ፍቅሬ ላይ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ክስ ለፖሊስ ያቀረበችው አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነች። ሠራዊት ፍቅሬ ግን፤ በመድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት መወራቱን በተመለከተ ተጠይቆ፤ “በሬ ...
Read More »የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያድረጉ ነው
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እሁድ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱም ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አጠንክረው አሰሙ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 13 ወራት ዘወትር አርብ ተቃውአቸውን ያለመሰልቸት በጽናት እያሰሙ ያሉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፣ ዛሬም ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲያሰሙ አርፍደዋል። በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ደሴ ፣ ስልጤ እና ሌሎችን ከተሞች በድምጽ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ወትሮ ተቃውሞ የሚደረግበት ታላቁ አንዋር መስኪድ ጭር ብሎ ፒያሳ የሚገኘው ኑር መስጊድ በሰዎች ተጨናንቆ አርፍዷል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ ...
Read More »ኢህአዴግ ለ2002ቱ ምርጫ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማውጣቱን አንድ ሪፖርት አጋለጠ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ በዓለም የምርጫ ታሪክ እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ 99 ነጥብ 6 በመቶ በማሸነፍ ወደ አውራ ፓርቲ ተሸጋግሬበታለሁ ባለው የ2002ቱ ምርጫ በድምሩ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ከግንባሩ የተገኘ ሪፖርት አመለከተ፡፡ ይህ ገንዘብ የኢትዮጵያ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለምርጫ ቦርድ በቀጣይ ወር ለሚያካሂደው የአካባቢና የአዲስአበባ ምርጫን ጨምሮ ለመደበኛ በጀት ከፈቀደለት 19 ነጥብ 8 ...
Read More »በኣዲስ ኣበባ ከባለቤቶቹ ፈቃድ ውጪ የቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃበር እየታረሰ ነው
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፒያሳ እስከ ጎፋ ካምፕ ድረስ ሊሠራ ከታሰበው የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ፥ የ ቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃብር ስፍራ ከሙታን ቤተሰብ አውቅና ውጭ እየታረሰ እና የሙታን ኣጽምም ከአፈር ጋር እየታፈሰ ወጣ ወዳለ ስፍራ እየተጣለ እንደሆነ ታውቋል። ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በልማት ስም እየተካሄደ ያለውን ይህን ዘግናኝ ድርጊት እያስፈፀመ ያለው የመንገድ ሥራውን በበላይነት እየሠራ ያለው የመንገዶች ባለስልጣን ...
Read More »የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለድርጅታዊ ጉባኤ መቀሌ ገብተዋል
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካለፉት 21 አመታት ጀምሮ የመንግስትን ስልጣን በበላይነት የያዘው ህወሀት፣ ድርጅቱን ለረጅም ጊዜ የመሩት አቶ መለስ ዜናዊ ካረፉ በሁዋላ ያጋጠመውን የመከፋፈል አደጋ ሸፋፍኖ በማለፍ፣ ከመጋቢት 8 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት 11ኛ ጉባኤውን የሚያካሄድ ሲሆን፣ በጉባኤው ለመሳተፍ ነባር አመራሩ መቀሌ መግባታቸው ታውቋል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ...
Read More »