በጄኔቭ በተመድ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ከነገ በስቲያ ማርች 20፣ 2013 በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ት ቤት ፊት ለፊት ኢህአዴግ በእመነት ተቋማት ላይ እአካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ ሙስሊም ወገኖች ያቀረቡትን የእመነት ነጻነት ጥያቄ ወደ ጎን መግፋቱን በመቃወም እና የሚካሄድባቸውን አፈናና ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹህን ዜጎች ላይ የሚካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም፣ በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት አስከፊና አሳዛኝ ሁኔታ የዳረጋትን አገዛዝ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፉ እንደሚካሄድ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሎአል።

ሰልፉ በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በ13 ሰአት ይካሄዳል።