የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያድረጉ ነው

መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ  ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እሁድ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱም ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡