መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ለጀመሩት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ከኤርትራ መንግስት ለሚሰነዘር ማንኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል። የኤርትራ መንግስት አስታጥቆ የላካቸውን የ ግንቦት7 ፣ ኦብነግና ኦነግ ጥቃቶችን መከላከላቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በዚህ አመትም ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። ዶ/ር ...
Read More »Author Archives: Central
በአማራ ክልል በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች አብድራፊ ወደ ትግራይ ክልል ሊካተት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገለጹ
መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአሁን ቀደም ከትርፍ አምራች የአማራ ክልል ወረዳዎች ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉ ቦታዎች አሁም ድረስ በሁለቱ ክልሎች መካከል የውዝግብ ምክንያት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የአብደራፊ ከተማን ወደ ትግራይ ክልል ለመጠቅለል የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ስጋት አሳድሮብናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል። የክልሉ መሪዎች ለአጎራባች ክልል ኢንቨስተሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሆኑ የእርሻ መሬቶችን ...
Read More »የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አንድ ባለስልጣን መግደሉን አስታወቀ
መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በወሰደው እርምጃ የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣ ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል ብሎአል። ህዝብን እየበደሉ ባሉ የስርዓቱ ታጣቂዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንባሩ አስጠንቅቋል። ኢሳት የመተማ ገንዳውሃ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ ...
Read More »በአዲስ አበባ የዕንቁላል ምርቶች እጥረት አጋጠመ
መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የዕንቁላል ምርቶች እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በአስደንጋጭ ፍጥነት እያሻቀበ መሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጸዋል፡፡አንዳንድ አምራቾች በበኩላቸው እጥረቱ ያጋጠመው ከመኖ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተዘዋወርንባቸው ሳሪስ፣ ሾላ እና ካዛንቺስ አካባቢዎች በበርካታ መደብሮች የዕንቁላል ምርቶች ሰሞኑን ጨርሶ የሌለ ሲሆን አቅርቦቱ ባለባቸው መደብሮች የአንድ አበሻ ዕንቁላል ዋጋ ከ3 ብር ከ25 ...
Read More »አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን የደህንነት ሰራተኛ ከአገሯ መባረሩዋን አረጋገጠች
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለተቃውሞ ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በተጓዙት ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው የኢምባሲ ሰራተኛ በ48 ሰአታት ውስጥ አገር ለቆ እንዲወጣ መደረጉን ኢሳት በሰበር ዜና መዘገቡን ካስታወቀ ከአንድ ቀን በሁዋላ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግለሰቡ ከአገር መባረሩን አረጋግጧል። የኢትዮጵያ መንግስት በቅጽል ስሙ ወዲ አይኑ የተባለውን የደህንነት ሰራተኛ የዲፕሎማቲክ ከለላ እንዲያነሳ ቢጠየቅም፣ ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ከአገር ለቆ ...
Read More »በኦጋዴን ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ መሆኑን ኦብነግ አስታወቀ
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ( ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚታየው ድርቅ እየተባባሰ በመሄዱ ነዋሪዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው። ለተከታታይ ሁለት አመታት የቀጠለው ድርቅ በመንግስት ከተጣለው የኢኮኖሚ ማእቀብ ጋር ተያይዞ በነዋሪው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። የአለማቀፉ ማህበረሰብ ለአካባቢው ህዝብ የሚሰጠው እርዳታ በተገቢው ቦታ ላይ መድረሱን እንዲያረጋጋጥ ኦብነግ ጠይቋል። ሸበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ዛሬ መስከረም 23/2007 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አራዳ ችሎት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ፡ የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ለአንድ ወር ከ15 ቀን ያህል ከታሰሩ በሁዋላ ከ3 ...
Read More »አንድ መምህር ጠንካራ ጥያቄዎችን ብቻ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን ገለጹ
መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ለመምህራን እየሰጠ ባለው የፖለቲካ ስልጠና ላይ የሚሳተፉት በወሊሶ ከተማ አስተማሪ የሆኑት ግለሰብ “ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን” ተከትሎ መታሰራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። መምህሩ እንዳሉት ” የመንግስት ባለስልጣናት መሬት እየከፋፈሉ መሸጣቸውን አስመልክቶ ማስረጃ አቅርበው በመጠየቃቸው” ህዝብን “ልታነሳሳ ነው” በሚል ለአንድ ቀን ታስረው ” ሁለተኛ እንዳትናገር በሚል በማስጠንቀቂያ መፈታታቸውን ተናግረዋል። ማስጠንቀቂያው ከተሰጣቸው በሁዋላ ጥያቄ መጠየቅ ማቆማቸውንም ...
Read More »የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛው እጣ ፋንታ አልታወቀም
መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት ሰኞ በኦጋዴንና በጋምቤላ በተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮችን ለማነጋገር በኢምባሲው አካባቢ በተገኙት ኢትዮጵያውያን ላይ አንድ የስልጣን ደረጃው ያልታወቀ ሰለሞን ወይም በበረሃ ስሙ ወዲ ወይኒ የተባለ ግለሰብ ጥይቶችን በመተኮሱ የኢትዮጵያውያንንና አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል። አለማቀፍ እውቅና ያላቸው ሮይተርስ እና ዋሽንግተን ፖስት የመሳሰሉ የዜና አውታሮች ዜናውን በድረገጾቻቸው ይዘው የወጡ ሲሆን፣ የከተማዋ ...
Read More »የወግዲ ወረዳ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የመሰናዶ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ መመህራን የስራ ማቆም አድማውን ያደረጉት መንግስት ቃል በገባው መሰረት የሃምሌ እና ነሃሴ ወር ደሞዝ ጭማሪ አልከፈለንም በሚል ነው። መመህራኑ የደሞዝ ጭማሪው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በታየው የዋጋ ንረት እየተሰቃየን ነው በማለት የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አስተዳዳሪው ለስብሰባ በሜዳቸው ሳይሳካለቸው ቀርቷል። እርሳቸውን የወከሉት አቶ ሃጎስ ...
Read More »