በኦጋዴን ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ መሆኑን ኦብነግ አስታወቀ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ( ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚታየው ድርቅ እየተባባሰ በመሄዱ ነዋሪዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው። ለተከታታይ ሁለት አመታት የቀጠለው ድርቅ በመንግስት ከተጣለው

የኢኮኖሚ ማእቀብ ጋር ተያይዞ በነዋሪው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

የአለማቀፉ ማህበረሰብ ለአካባቢው ህዝብ የሚሰጠው እርዳታ በተገቢው ቦታ ላይ መድረሱን እንዲያረጋጋጥ ኦብነግ ጠይቋል። ሸበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች እንደደረሱት የገለጸው ኦብነግ፣ በሁሉም የኦጋዴን አካባቢዎች ደግሞ

እንስሳት እየሞቱ ነው ብሎአል።