የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ዛሬ መስከረም 23/2007 ዓ.ም  ከሰዓት በኋላ አራዳ ችሎት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ለአንድ ወር ከ15 ቀን ያህል ከታሰሩ በሁዋላ ከ3 ሳምንታት በፊት ወደ ማእከላዊ ተዛውረዋል።