አንድ መምህር ጠንካራ ጥያቄዎችን ብቻ  በመጠየቃቸው መታሰራቸውን ገለጹ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ለመምህራን እየሰጠ ባለው የፖለቲካ ስልጠና ላይ የሚሳተፉት በወሊሶ ከተማ አስተማሪ የሆኑት ግለሰብ “ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቃቸውን” ተከትሎ መታሰራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

መምህሩ እንዳሉት ” የመንግስት ባለስልጣናት መሬት እየከፋፈሉ መሸጣቸውን አስመልክቶ ማስረጃ አቅርበው በመጠየቃቸው” ህዝብን “ልታነሳሳ ነው” በሚል  ለአንድ ቀን ታስረው ” ሁለተኛ እንዳትናገር በሚል በማስጠንቀቂያ መፈታታቸውን ተናግረዋል።

ማስጠንቀቂያው ከተሰጣቸው በሁዋላ ጥያቄ መጠየቅ ማቆማቸውንም አክለው ገልጸዋል