Author Archives: Central

በንብረት ላይ ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ሊወሰድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) የአማራ ክልላዊ መንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫም ንብረት ላይ ጥፋት የፈጸሙ ሰዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል። በወልዲያ፣መርሳና ቆቦ የተገደሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በተመለከተ ግን ለህግ የሚቀርብ አካል ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም። ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል በማለት የተሰጠው መግለጫ ብዙዎችን ማስቆጣቱ ተሰምቷል። የአማራ ክልል መንግስት ...

Read More »

በአዳማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) በአዳማ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ተገለጸ። ህገወጥ ቤት ለማፍረስ የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመቃወም በተደረገው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። መንገዶች በድንጋይና በእንጨት ተዘግተው እንደነበር የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች ወደ አመጽ የተቀየረውን የህዝቡን ተቃውሞ ለማስቆም የፖሊስ ሃይል ቁጥሩን ጨምሮ መሰማራቱን ገልጸዋል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውም ታውቋል። በአዳማ/ ናዝሬት ዛሬ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ህገወጥ ቤት ለማፍረስ በከተማዋ ...

Read More »

የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቤተሰቦች ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቤተሰቦች ሳውዳረቢያ ውስጥ ታሰሩ። የቢሊየነሩ ተውልደ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የታሰሩት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በድርድር ገንዘብ ከፍለው ከእስር እንዲወጡ የቀረበላቸውን አማራጭ ባለመቀበላቸው እንደሆነም ተመልክቷል። የሳውዳረቢያ መንግስት በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ባለሃብቶች አንዱ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼህ መሀመድ አላሙዲን በህዳር ወር ሳውዳረቢያ ሪያድ ውስጥ መታሰራቸው ይታወሳል። በእሳቸው የተጀመረው እስር ደግሞ በቤተሰቦቻቸውም ላይ መቀጠሉን ነው ሚድል ኢስት ሞኒተር ትላንት ...

Read More »

ሁሉን ያቀፈ ሀገራዊ ጉባዔ እንዲጠራ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በኢትዮጵያ ሁሉን ያቀፈ ሀገራዊ ጉባዔ እንዲጠራ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ማህበር ጥሪ አቀረበ። ማህበሩ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የተመለከተ ባለ 34 ገጽ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ጠመንጃ ያነሱ የነጻነት ሃይሎች፣ በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሚመለከታቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተሳታፊ የሆኑበት ጉባዔ በመጥራት ኢትዮጵያን ከተደቀነባት ሀገራዊ ቀውስ መታደግ ይገባል ሲል ማህበሩ አስታውቋል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ አፈናዎች፣ ግድያዎችንና መጠነ ሰፊ ...

Read More »

የወልቃይት ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በወልቃይ የወርቅ ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ የወልቃይት ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተገልጸ። ልዩ ስሙ ኢድሪስ በሚባል የወርቅ ክምችት በሚገኝበት ስፍራ በወርቅ ቁፋሮ ስራ በተሰማሩ የወልቃይት ተወላጆች ላይ ድብደባውን የፈጸሙት በትግራይ ፖሊሶች የታገዙ በአካባቢው በሰፈሩ ሰዎች መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በወልቃይት የማይጸብሪ ከተማ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ተቃውሞው በማንነታችን በእኩል እየታየን አይደለም በሚል እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ...

Read More »

በሰሜን ወሎ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በሰሜን ወሎ ያለው ውጥረት መቀጠሉ ታወቀ። በብአዴን አመራሮች የሚጠሩ ሰብሰባዎችም እየተበተኑ መሆኑ ተሰምቷል። ከቆቦ ጀምሮ እስከ መርሳ ዛሬ መንገዶች ዝግ ናቸው። ከቆቦ ወደ ትግራይ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች በወታደሮች ታጅበው መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወልዲያ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ወታደሮች በህዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸሙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከመርሳና ወልዲያ በትንሹ 500 ወጣቶች በአፋር ጭፍራ በረሃ ተወስደው በስቃይ ላይ ...

Read More »

የወይዘሮ አዜብ መስፍን የውስጥ ሪፖርት ከአመታት በኋላ ተጋለጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት የሆኑ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እንዲሁም ሌሎች ኩባንያዎችን በተመለከተ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረቡት የውስጥ ሪፖርት ከአመታት በኋላ ተጋለጠ። በሃገሪቱ ህግ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይኖረው ይከለክላል። ይህ ባለ 92 ገጽ ሪፖርት የሕወሃት ኩባንያዎችን ዝርዝር አፈጻጸምና ገቢያቸውን የተመለከተ እንደሆነም መረዳት ተችሏል። ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሪፖርት ...

Read More »

ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰየሙ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የኬንያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪና ዕጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ ፈጸሙ። በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት ቃለ መሃላውን ሲፈጽሙ ለማሰራጨት የተዘጋጁት የሀገሪቱ ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጸጥታ ሃይሎች ተዘግተዋል። ይህን ተከትሎም በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውጥረት መስፈኑን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የ72 አመቱ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ በናይሮቢ ኡሁሩ ፓርክ ቃለ ...

Read More »

መለስተኛ የበረራ ሰራተኞች ላይ እገዳ ተጣለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ መለስተኛ የበረራ ሰራተኞቹን ወደ አሜሪካና ካናዳ እንዳይበሩ እገዳ መጣሉ ተነገረ። አየር መንገዱ የበረራ ሰራተኞቹ ወደ አሜሪካና ካናዳ እንዳይበሩ የከለከለው ወደ ሁለቱ ሀገራት የሚመጡ ባልደረቦቹ በመጡበት ጥገኝነት እየጠየቁ በመቅረታቸው ነው። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ወር ብቻ 21 የበረራ ሰራተኞች ለስራ በወጡበት በካናዳና አሜሪካ ቀርተዋል። እናም የአየር መንገዱ መለስተኛ የበረራ ሰራተኞች በተለይ በአሜሪካና በካናዳ ለስራ እንደወጡ ...

Read More »

ኤች አር 128 ለድምጽ አሰጣጥ ሊቀርብ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በአሜሪካ ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ ሕገ ውሳኔ በምክር ቤቱ ለድምጽ አሰጣጥ እንደሚቀርብ ታወቀ። ሕገ ውሳኔው ለድምጽ አሰጣጥ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት መርማሪዎች በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያጣሩ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የማይፈቅድ ከሆነ ነው። የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከሌሎች የማህበረሰቡ ተወካዮችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ትላንት ከአሜሪካ ምክር ...

Read More »