(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011) በትግራይ አዲግራት ከተማ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸው ቁጣን አስነሳ። ክልሉን የሚያስተዳድረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህገወጥ ናቸው በሚል ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱ ታውቋል። ተጨማሪ መኖሪያ ቤቶችም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በትግራይ የእንደርታ ተወላጆች ላይ የክልሉ መንግስት በደል እየፈጸመ ነው በሚል ተቃውሞ ተነስቷል። በመቀሌ ባለፈው ሳምንት በእንደርታና በመቀሌ እግርኳስ ቡድን ደጋፊዎች መሃል በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ...
Read More »Author Archives: Central
በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ተማሪዎችና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011)በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ 10 በላይ ተማሪዎች ተጎድተው በሀረር ህይወት ፋና ሆስፒታል እንደሚገኙ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ ። የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በሀረር ስታዲየም የገቢ ማሳባሰቢያ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎቹ አዲስ አባባ የኦሮሞ ናት በሚል ሰልፍ በማድረግ የዩኒቨርስቲውን ንብረት መሰባበራቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞም ትምህርት መቋረጡና ተማሪዎቹም ወደተለያዩ አካባቢዎች መሸሻቸው ተሰምቷል። ...
Read More »በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየደረሰ አይደለም
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011) በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየደረሰ አለመሆኑ ተገለጸ። በአካባቢው በቅርበት ጉዳዩን የሚከታተሉት አካላት ለኢሳት እንደገለጹት በአካባቢው እየጣለ ካለው ዝናብ ጋር በታያያዘ የሟቾቹ ቁጥር ጨምሯል። ለሚመለከተው አካል ጉዳዩን በተደጋጋሚ ቢያሳውቁም ያገኙት ምላሽ እንደሌለ ነው ለኢሳት ካደረሱ መረጃ ማወቅ የተቻለው። የአካባቢው ባለስልጣናት መረጃ ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ደግሞ ችግሩን የከፋ አድርጎታል ብለዋል የኢሳት የመረጃ ምንጮች።
Read More »የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር ኤርምያስ አስገዶም በተተኮሰበት ተገደለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 30/2011) በአባቱ ኤርትራዊ ደም ያለውና የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር ኤርምያስ አስገዶም (ኒፕሲ ሐስል) በተከፈተበት ተኩስ መገደሉ ተነገረ። የ33 ዓመቱ ራፐር በርካታ ቦታዎች ላይ በጥይት መመታቱን እና ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ኤርምያስ አስገዶም (ኒፕሲ ሐስል) ሎስአንጄልስ ወስጥ በባለቤትነት በሚያስተዳድረው ማራቶን የአልባሳት መደብር በስድስት ጥይት ተበሳስቶ ሲገደል ሌሎች ሁለት ሰዎችም በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለዋል። ከኤርትራዊ አባት እና ...
Read More »ኢሶዴፓ የፓርቲውን ስያሜ እና የመተዳደሪያ ደንብ እንደሚያሻሽል ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 30/2011) የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የፓርቲውን ስያሜ እና የመተዳደሪያ ደንብ እንደሚያሻሽል ተገለጸ። የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አህመደ ሺዴ ጉባኤው ፍትህ ዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት በክልሉ ለማረጋገጥ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ አህመደ ሽዴ እንዳሉት በተመዘገበው ሃገራዊ ለውጥ በክልሉ ጠንካራና ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ሃሳብን ...
Read More »የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ማምረት ካቆመ አራት ወራት ማስቆጠሩ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 23/2011)የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ማምረት ካቆመ አራት ወራት ማስቆጠሩን በፋብሪካው ተቀጥረው የሚሰሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንዳሉት ፋብሪካው ለምን ተዘጋ ለሚለው ጥያቄያችን ምላሽ ማግኘት ባለመቻላችንም ወደ ፋብሪካው የሚወስደውን መንገድ ዘግተናል። መንገዱ ከተዘጋም አራት ቀናትን አስቆጥሯል ብለዋል። ዋነኛ ጥያቄያችንም ይላሉ ፋብሪካውን እየመሩ ያሉት ሰዎች ትላንት ፋብሪካውን ሲመዘብሩ የነበሩ ስለሆኑ ከቦታቸው ይነሱ፣ ፋብሪካውም በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ገብቶ እኛም ሃገራችንም ...
Read More »የብሔራዊ ባንክ በቀጣዮቹ ወራት የውጭ ምንዛሪ እንደማይኖር አስታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 30/2011)በቀጣዮቹ ወራት ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በዘለለ ለኢኮኖሚው የሚሆን የውጭ ምንዛሪ እንደማይኖር የብሔራዊ ባንክ ገዥው ዶክተር ይናገር ደሴ አስታወቁ። የብሔራዊ ባንክ ገዥው ዶክተር ይናገር ደሴ የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት ባለፉት 8 ወራት ብቻ የ8.9 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሚታይ ተረጋግጧል። የባንኩ ገዥ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ባለፉት ስምንት ...
Read More »በእነ አቶ በረከት ስምኦን መዝገብ የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2011)የባህርዳርና የአካባቢው ፍርድ ቤት በእነ አቶ በረከት ስሞዖን መዝገብ ለአቃቤ ህግ ተጨማሪ የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ። የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በድጋሚ የጠየቁት ተጠርጣሪዎቹ በክስ መመስረቻው ወቅት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡና እስከዛው ግን በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ችሎቱ አዟል። ችሎቱ በእነ አቶ በረከት ጉዳይም አቃቤ ህግ ህጉ በሚፈቅደው ጊዜ ውስጥ ክስ እንዲመሰርት በማዘዝ፥ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የመጠየቂያ መዝገቡን ዘግቷል። የአማራ ክልል የፀረ ሙስና ...
Read More »በአፋር ክልል ከ3 ሺ እስከ 5ሺ በሚሆኑ ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2011) በአፋር ክልል ከ3 ሺ እስከ 5ሺ በሚሆኑ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ። የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ በክልሉ በተፈጸመው ጥቃት አንድ መንድር በእሳት መቃጠሉን ተናግረዋል። ግዛትን የማስፋፋት ጥቃት ነው እየደረሰ ያለው የሚሉት አቶ ጋአስ ጥቃቱ በሶማሌ ላንድ፣በጅቡቲና በአልሻባብ ታጣቂ ሃይሎች እየተፈጸመ መሆኑን ነው የተናገሩት። ክልሉ እየደረሰበት ያለውን ጥቃት ለፌደራል መንግስቱ በተደጋጋሚ ቢያሳውቅም ምንም ያገኘው ምላሽ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከእስክንድር ነጋ ጋር ለመወያየት እንደሚፈልጉ ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2011) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ታጋዩ እስክንድር ነጋ ጋር ለመወያየት እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ዶክተር አብይ አህመድ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስመልክቶ ከ40 በላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፥ምሁራን እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች በጽሁፍ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። እስክንድር ነጋን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ሰብአዊ መብትም እንዲከበር ያደረገውን አስተዋጽኦ እኔም የማደንቀው ነው ብለዋል። ባነሣቸው ሐሳቦች ምክንያት በመንግሥት በኩል በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ...
Read More »