በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ተማሪዎችና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011)በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ 10 በላይ ተማሪዎች ተጎድተው በሀረር ህይወት ፋና ሆስፒታል እንደሚገኙ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ ።

የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በሀረር ስታዲየም የገቢ ማሳባሰቢያ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎቹ አዲስ አባባ የኦሮሞ ናት በሚል ሰልፍ በማድረግ የዩኒቨርስቲውን ንብረት መሰባበራቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞም ትምህርት መቋረጡና ተማሪዎቹም ወደተለያዩ አካባቢዎች መሸሻቸው ተሰምቷል።