በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየደረሰ አይደለም

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011) በጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየደረሰ አለመሆኑ ተገለጸ።

በአካባቢው በቅርበት ጉዳዩን የሚከታተሉት አካላት ለኢሳት እንደገለጹት በአካባቢው እየጣለ ካለው ዝናብ ጋር በታያያዘ የሟቾቹ ቁጥር ጨምሯል።

ለሚመለከተው አካል ጉዳዩን በተደጋጋሚ ቢያሳውቁም ያገኙት ምላሽ እንደሌለ ነው ለኢሳት ካደረሱ መረጃ ማወቅ የተቻለው።

የአካባቢው ባለስልጣናት መረጃ ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ደግሞ ችግሩን የከፋ አድርጎታል ብለዋል የኢሳት የመረጃ ምንጮች።