ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ በ11ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ሩጫ ላይ ሲሳተፉ በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ፖሊስ ጣቢያዎች በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን በርካታ ወጣቶች ከማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በዋስ መፍታት ጀመረ እሁድ ህዳር 17 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ታላቁ ሕዝባዊ ሩጫ ላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ...
Read More »Author Archives: Central
ከኢትዮጵያ ተዘርፎ በውጭ አገር ባንኮች የተቀመጠው 11 ቢሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ እንዲመለስ አንድ ታዋቂ ምሁር ገለጡ
ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአካውንቲግና የፋይናንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ሚንጋ ነጋሽ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ በህግ፣ በወነጀል ምርመራ እና በተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህን ገንዘብ ለማስመለስ በአንድነት ሆነው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ። ችግሩ በአንድ በኩል መንግስት በፖለቲካውና በንግዱ ውስጥ ጣልቃ መግባቱ የፈጠረው መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ሚንጋ፣ ሌሎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዋነኝነት የሚያሽከረክሩት ኢፈርትና ...
Read More »አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እና ብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ውህደታቸውን አጽድቀው አንድ ውህድ ፓርቲ በመመስረት የፓርቲ ሊቀመንበር እንደሚመርጡ አስታወቁ
ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ ቅዳሜ እና እሁድ በዲአፍሪክ ሆቴል 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያካሂድና ውህደቱን የሚያጸድቅ ሲሆን ፣ ብርሃን ለአንድነት ፓርቲ ደግሞ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ የፓርቲው ህልውና ይከስማል በአዲሱ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የፓርቲው ሊቀመንበር በቀጥታ በጠቅላላ ጉባዔ የምረጣል። የፓርቲውን ካቢኔ መርጦ በብሄራዊ ምክር ቤት ይሁንታ አስጸድቆ የሊቀመንበሩም ሥልጣን ...
Read More »በአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ተጠናክሮአል ተባለ፣ የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንም በየቤታቸው እየተፈተሹ ነው
ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመዲናይቱ በሚገኙ ትላልቅ ፎቆችና ዋና ዋና መንገዶች ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ በመባል የሚታወቁት ተወርዋሪ የጥበቃ ኃይሎችና የደህንነት አባላት ሩጫ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ እየታየ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ዛሬ ዘገባ፤የፌደራል ፖሊሶቹ በየመንገዱ ዜጎችን በማስቆምና “ተለጠፍ“ በማለት ልዩ ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ። የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን በየቤታቸው በሚመጡ ሦስት የፌደራል ፖሊስ አባሎች ልዩ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥን ቀደም ብሎ ይጠቀምበት የነበረውን የኢንተርኔት ቀጥታ ስርጭት ማሳያ ቲቪዩ ፕለየሩን ወደ ፍላሽ ፕለየር ቀየረ
ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ሲል ኢሳትን በኢንተርኔት ለመከታተል ቲቪዩ ፐልየር ሶፍት ዌርን መጫን ግዴታ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ አሰራር ግን በማንኛውም ኮምፒዩተር በፍላሽ ፕሌየር ስርጭቱን ለማየት ይቻላል። በርካታ ኢትዮጵያውያን አሰራሩን በተመለከተ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።የኢሳት ማኔጅመንት ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ቲቪዩ ፕለየር የተባለውን ሶፍትዌር ሳይጭኑ በየትኛውም ኮምፒዩተር ላይ በቀጥታ መመልከት የሚያስችላቸውን አሰራር ዘርግቷል። ቀጥታ ስርጭታችንን እንደተለመደው በ ...
Read More »ደጃዝማች ዘውዴ ገብረስላሴ መለስ ዜናዊ የትግራይ አይሁዶችን ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመው እንደነበር ተገለጠ
ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ የታሪክ ባለሙያ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ኢትዮጵያን ያገለገሉት፣ ከሶስት አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ደጃዝማች ዘውዴ ገብረስላሴ ፣ የመለስ ፖሊሲ አገሪቱን እንደማይጠቅማትና ለትግራይ ህዝብም አደገኛ መሆኑን ተናግረው እንደነበር፣ ከእርሳቸው ጋር ቅርበት የነበራቸው ሰው ገለጠዋል። ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉት ምንጫችን እንደተናገሩት፣ ደጃዝማች ዘውዴ ይህን የተናገሩት በዶ/ር ክንፈ አብረሀ ይመራ የነበረውንና አሁን አቶ ስብሀት ...
Read More »የምስራቅ ጎጃም ህዝብ በኢህአዴግ ባለስልጣናት ላይ ያለውን ተቃውሞ ገለጠ
ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በአማራ ክልል “የህዝብን ቅሬታ ለማስታገስ” በሚል ምክንያት ፣ ብአዴን በክልሉ ያካሄደው ግምገማ ንቅናቄው ያልጠበቃቸው ነገሮች በመከሰታቸው ግምገማውን ለመሰረዝ ተገዷል። በምስራቅ ጎጃም ዞን በተካሄደው ህዝባዊ ግምገማ ህዝቡ “ኢህአዴግ የ ችግርና መከራ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ለአገሪቱ ያመጣም ምንም ነገር የለም” በማለት በድፍረት መናገሩን ዘጋቢያችን ገልጧል። በተለይ የደብረ ኤሊያስ አካባቢ የመኢአድ ደጋፊዎች “ተቃውሞዓችን በሙስና ከተዘፈቀ ስርአት ...
Read More »ክረምቱ ሲገባ የአረቡ አብዮት ወጀብ ወደ ኢትዮጵያ እየነፈሰ ነው ሲል ረዩተርስ ዘገበ
ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የረዩተርሱ ጆን ሊዮልድ ባቀረበው ሰፊ ዘገባ በአረቡ አለም የተጀመረው ህዝባዊ ማእበል ፣ ወደ ጥንታዊቷ የስልጣኔ ማእከል ፣ ኢትዮጵያም፣ እየገሰገሰ ነው። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ካለፈው የሰኔ ወር ጀምሮ ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላትን ማዋከብ ፣ ማሰርና አገር ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጋቸውን ረዩተርስ ገልጣዐል። በቅርቡ የስደትን ጎራ ከተቀላቀሉት መካከል የሲፒጄ የነጻነት ተሸላሚ የአውራምባ ...
Read More »የፌዴራል ፖሊስ መርማሪዎች በፖለቲካ እሥረኞች ላይ የማሰቃያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ምንጮቻችን አስታወቁ
ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪዎች በፖለቲካ እሥረኞች ላይ የተለያዩ የማሰቃያ ወይም የቶርቸር ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ምንጮቻችን አስታወቁ፡ ለታሳሪዎች ከቤተሰብ የሚመጣውን የዘወትር ምግብ ደግሞ በአብዛኛው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ለእራሳቸው እንደሚመገቡት ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ወዲህ በከተሞችና በክልሎች አካባቢ በሚነሱ የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጥያቄዎች የደህንነት ሠራተኞችና የፌዴራል መንግሥት ፖሊሶች በቁጥጥር ...
Read More »ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደመወዛችን አይቆረጥብንም ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ” ጸረ-ሰላም ሀይሎች ” የሚል ደብዳቤ እየደረሳቸው ነው
ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደመወዛችን አይቆረጥብንም ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ” ጸረ-ሰላም ሀይሎች ” የሚል ደብዳቤ እየደረሳቸው ነው። የተለያዩ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ለኢሳት የደቡብ ዘጋቢ እንደገለጡት፣ የኢትዮጵያ የሰራተኛ አሰሪ አዋጅ አንድ ሰው ደመወዙን ያለራሱ ፈቃድ ወይም ያለፍድር ቤት ትእዛዝ እንደማይቆረጥበት ተደንግጎ ቢገኝም፣ መንግስት ግን ከሰራተኞች ላይ በግዳጅ እንዲቆረጠ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ...
Read More »