መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንደተደረገ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን የዘገቡ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ግን ምርጫው አልተሳካም ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያነጋገርናቸው ኢትዮጳያዊያን ሙስሊሞች ተናገሩ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምርጫው በተጀመረ በጥቂት ሰኣታት ውስጥ ለምርጫው ከተመዘገበው 7 ሚሊዮን ህዝበ ሙስሊም ውስጥ 95 ከመቶው ድምጹን እንደሰጠ ሲናገሩ፤ ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው ሙስሊሞች ግን፤ በምርጫው ...
Read More »የመድረክ አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር፤ የተሳካ ውይይት አደረጉ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር፤ ትናንትና እሁድ መስከረም 27 ቀን የተሳካ ውይይት አደረጉ። ላለፉት 3 ሳምንታት ከሲያትል ጀምረው በአትላንታና ዴንቨር እንዲሁም ሚኒያፖሊስ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ስብሰባ ሲያደርጉ የቆዩት፤ የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባላት፤ ፕ/ር መረራ ጉዲና፤ አቶ ስዬ አብርሀ፤ አቶ ተመስገን ዘውዴና አቶ ገብሩ አስራት በስብሰባው ላይ ተገኝተው ...
Read More »አቶ ከፍያለው አዘዘ እንደወጡ የቀሩት፤ ለስራ ወደ ዱባይ ከተላኩ በኃላ መሆኑን ሪፖርተር ዘገበ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩትና፤ ስርአቱን ከድተው አሜሪካ የገቡት አቶ ከፍያለው አዘዘ እንደወጡ የቀሩት፤ ለስራ ወደ ዱባይ ከተላኩ በኃላ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ ከፍያለው አዘዘ ወደ አሜሪካ መኮብለላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በመረዳቱም መኪናቸውን መረከቡንና፤ ስለ አቶ ከፍያለው መረጃ አልሰጠህም የተባለው ሹፌራቸውም ያለስራ እንዲቀመጥ መደረጉን ከሪፖርተር ዘገባ መረዳት ተችሏል። የአዲስ አበባ መገናኛ ...
Read More »አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባፉለት 21 አመታት ከድህነት ወለል በታች የነበረውን ህዝብ ከ38.7 ወደ 29.6 በመቶ መቀነስ ችለናል ሲሉ ተናገሩ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጨረሻም፤ የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባፉለት 21 አመታት ከድህነት ወለል በታች የነበረውን ህዝብ ከ38.7 ወደ 29.6 በመቶ መቀነስ ችለናል ሲሉ ተናገሩ። ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዛሬ ለተወካዮችና ለፌደሬሽን ምክርቤቶች አባላት በጋራ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ መንግስት አመታዊ በጀቱን ለመሸፈንና ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም፤ በብድርና በእርዳታ ገንዘብ ሲረዳ መቆየቱን ገልጸዋል። በተጻራሪው ከድህነት ወለል በታች የሚኖረው ...
Read More »የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት እንደሚያነሳ ታወቀ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሐሙስ ማምሻውን የተጠናቀቀው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ጁነዲን ሳዶ በመገምገም ከፓርቲ ኃላፊነታቸው እንዲነሱና ያለመከሰሰ መብታቸው እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሰረት በቀጣዩ ሳምንት የዓመቱን ሥራውን የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት ያለመከሰሰ መብታቸውን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ጁነዲን ከሳዑዲ ኤምባሲ ጋር ...
Read More »የኢህአዴግ ደጋፊዎች በእስራኤል አገር የሚገኙ አትዮጵያውያን ያካሄዱትን ስብሰባ ለማወክ ቢሞክሩም አልተሰካላቸውም ሲሉ አዘጋጆች ገለጡ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስራኤል አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ለመነጋገር፣ በእስራኤል አገር ስላለው የስደተኞች መብቶች ለመነጋጋር እንዲሁም በመገለላቸውና በዘረኝነት የተነሳ የመገለልና የባይተዋርነት ስሜት የሚሰማቸውን ቤተ እስራኤላውያንን ለመርዳት የተቋቋመው ማህበር ባለፈው አርብ ፣ እኤአ ኦክቶበር 5፣ 2012 በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ያደረገውን ስብሰባን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ለማሰናከል ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው በመቅረቱ በፖሊስ ተገደው ...
Read More »በጅቡቲ ለአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘናቸውን አልገለጹም የተባሉ ከ20 በላይ ኢትዮጵያውን ታፍነው ተወሰዱ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የታሰሩት የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ወቅት ደስታችሁን ገልጻችሁዋል ተብለው ነው። 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ እና በኢትዮጵያውያን የደህንነት ሰዎች ታፍነው በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ በደወሌ በኩል አድርገው ተወስደዋል። ከታሰሩት ወጣቶች መካከል ማሙሸት አንዳርጌ፣ ሰለሞን፣ ብዙአየሁ፣ ያሬድ በልበላ፣ አለማየሁ፣ ወንዶሰን፣ አንዳርጌ፣ ቴዎድሮስ፣ እንዲሁም ስማቸው ያለተገለጠ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል። ...
Read More »ላኪዎች ንግድ ፈቃዳችንን ለመመለስ ተገደናል እያሉ ነው
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“መንግሥት ዘርፉን ከማሳደግ ይልቅ በየጊዜው የሚያቆረቁዙ አሠራሮችን እየተከተለ ነው” ያሉ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች፤ ንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ እየተገደዱ መሆናቸውን ተናገሩ። እንደ ነጋዴዎቹ ገለፃ መንግስት በዘርፉ እየተከተለ ያለው አሠራር አገሪቱ ማግኘት ያለባትን የውጭ ምንዛሪም እንድታጣ ምክንያት ሆኗል። ላኪ ነጋዴዎቹ በመንግስት አሠራር ላይ ጠንካራ ተቃውሟቸውን ያሰሙት፤የአዲስ አበባ ንግድና ዘረርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባለፈው ...
Read More »በለገጣፎ እና በለገዳዲ አካባቢ የሚካሄደውን የመሬት ወረርሽኝን ለመገናኛ ብዙሀን ያጋለጡ ወጣቶች መታሰራቸውን ተከትሎ፣ የከተማው ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና ከእነርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ባለሀብቶች የሚያደርጉትን የመሬት ዝርፊያ ለመገናኛ ብዙሀን ያጋለጡ ወጣቶች መታሰራቸውን ተከትሎ ከ500 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። መኮንን ተስፋየ፣ ጌታቸው ተፈራ፣ ድርባ ጉዳ፣ ገመቹ ወርቁ፣ እንዳልካቸው መንግስቱ፣ ምትኩ ንጉና ሲሳይ አለሙ የተባሉት ወጣቶች መረጃዎችን ለአሜሪካ እና ለጀርመን ድምጾች ...
Read More »በእሁዱ የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ ሙስሊሙ በምርጫው እንዲሳተፍ እየተገደደ መሆኑን የተለያዩ ሙስሊሞች ገለጡ
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አወዛጋቢ የሆነው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ የአብዛኛውን ህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ እንዳልቻለ ነው ሙስሊሞች የሚናገሩት። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች ለኢሳት እንደገለጡት መንግስት ህዝቡን በማስፈራራት በምርጫው በግድ እንዲሳተፉ እያስገደደ ነው። በጅማ ነዋሪ የሆነች አንድ ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች ወጣት “ህዝቡ በምርጫው የሚሳተፈው አምኖበት ሳይሆን ተገዶ ነው ” ትላለች መንግስት በቀበሌ ቤቶች የሚኖሩትንም ሆነ ...
Read More »