አሜሪካ በሶሪያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መቃረቡዋን ተከትሎ የመካከለኛው ምስራቅ እንደገና በጦርነት ሊታመስ እንደሚችል ተሰግቷል።

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦባማ አስተዳደር በዜጎቹ ላይ የኬሚካል መሳሪያዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ባለው የባሽር አላሳድ መንግስት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ሲያስጠነቅቅ ከቆ በሁዋላ በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ፣ ጉዳዩን ለኮንግረስና ለሴኔት አቅርበው ለማስወሰን በመፈለጋቸው ባለፈው ሳምንት የታየው  የጦርነት ደመና ዝናቡን ሳያርከፈክፍ መጥፋቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንት ኦባማ የዲሞክራት እና የሪፐብሊካን መሪዎችን ከአነጋገሩ በሁዋላ ፣ ሁለቱም መሪዎች የሰጡዋቸው መልሶች አዎንታዊ ...

Read More »

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ...

Read More »

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፤

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋና እንደዘገበው ፤ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው ። ፋና ይህም ቢልም አቶ ወልደስላሴ ከደህንነት ዋና ሹሙ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ጠብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል። በተለይ መቀሌ በተካሄደው የህወሀት ጉባኤ ላይ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በአቶ ወልደስላሴ መካከል ...

Read More »

በመላ ሐገሪቱ ለህዝብ ተብለው የተገነቡ የኪራይ ቤቶች ድርጅት መኖሪያ ቤቶች በመንግስት ባለስልጣናት የተያዙ መሆናቸውን ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ባገኘው መረጃ በአዲስ አበባ የተገነቡ 2345 ቤቶች ለሚኒስትሮች እና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባለስልጣናት ተሰጥተዋል። የቤቶች ልማት ባካሄደው ጥናት ፣ አብዛኞቹ ባለስልጣናት የግል ቤቶቻቻውን በማከራየት በመንግስት ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ።  ኪራይ ቤቶች ቤቶቹን እንዲለቁ ሲጠይቃቸው በግል የገነቡዋቸው ቤቶች ለደህንነታቸው ዋስትና እንደማይሰጡ በመከራከር ቤቶቹን ለማስረከብ ፈቃደኞች አልሆኑም። በትግራይ ክልለ በመቀሌ 375 ...

Read More »

በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ተገለጠ

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩ -ኤርትራ ግጭት እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያው አልሸባብ ጋር ካደረገችው ጦርነት ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን የጦር ሃይሎች ሆስፒታል የስነ ልቦና ህክምና ቡድን መረጃ አመለከተ ከመዝገብ ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ፤ በጦርነቱ ስዓት በተከሰተ ምንነቱ ባልታወቀ የሞራል እና የስነ ልቦና ችግር ከ3 ሺ 500 በላይ ወታደሮች እስከ እብደት  በሚያደርስ በሽታ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ጥራት ደረጃ ሊሻሻል አለመቻሉ ተገለጸ

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት 3ኛው የአማራ ክልል ትምህርት ፊስትቫል ምክትል ጠቅላይ ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ፤የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሺጉጤ ፤ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ሲከፈት፣ ዶክተር ጸሐይ ጀምበሬ ባቀረቡት ጽሁፍ፣ የመንግስት ትምህርት ቤት አሰተዳደራዊ ችግር ለትምህርት ጥራት እንቅፋት እየሆነ መጥቱዋል ብለዋል።  ከአመቱ ውስጥ  260 ቀናት ይባክናሉ ያሉት ዶክተር ጽሐይ ኢትዮጵያ በትምህርት ጥራት ...

Read More »

በሞያሌ ከፈተኛ ግጭት መነሳቱ ተዘገበ

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞያሌ ከተማ  በገሪና በቦረና ጎሳዎች መካከል ከሳምንታት በፊት የተነሳው ግጭት እንደገና አገርሽቶ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው። የኬንያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ወደ አካባቢው በመላክ ግጭቱን ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ቢናገርም ችግሩ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የኬንያ ጋዜጦች አየዘገቡ ነው። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ20 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። በአካባቢው የሚገኙ የንግድ ቤቶች  ሲወድሙ ትራንስፖርትም ቆሟል። ...

Read More »

ወታደራዊ ትጥቅማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት

ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡ ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ይወጣሉ

ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተካሄደ ያለውን የሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ የማፈን ተግባርን በመቃወም ነገ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ አካላት ለኢሳት ገለጹ፡፡ የአርብ የፀሎትና የስግደት ስነ ስርዓትን ተከትሎ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በሀገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የመንግስት እርምጃ ለማውገዝ ያለመ እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሰይድ አብዱራህማን ተናግረዋል፡፡ የሙስሊሙን ጥያቄ ለማፈን ...

Read More »

ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ...

Read More »