መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ በሚሰጠው ስልጠና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለ10 ቀናት ተዘግተዋል።
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ ባለስልጣናቱ ስልጠና ላይ ናቸው የሚል ...
Read More »ደቡብ ሱዳን የአብየ ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ አለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበች
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር ማለትም በጥቅምት ወር ይካሔዳል ቢልም ...
Read More »ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ።
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሦስተኛው የ ኢህአዴግ ፕሬዚዳንት በመሆን በ አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ምትክ ተሾሙ። የኢህአዴግ/ኦህዴድ አባል የሆኑት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን በመተካት ሁለተኛው ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ በስፋት የተወራ ቢሆንም፤”ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚመረጠው ሰው የማናቸውም ፓርቲ አባል ያልሆነ ገለልተኛ ሰው መሆን አለበት” የሚል መመሪያ በማውጣት የግል ...
Read More »በአፋር የክልል የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እየተካሄደ ነው
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በክልሉ ከመልካም አስተዳደር እና ከሰዎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የሚታየው ችግር እየተባባሰ በሚገኝበት ሁኔታ የክልሉን ባለስልጣናት ለመምረጥ በአዋሽ አርባ ታንከኛ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄ ነው። ከፍተኛ የህወሀት ድጋፍ አላቸው የሚባሉት የአቶ እስማኤል አሊሴሮ ደጋፊዎች በአንድ በኩል ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሰዎች በሌላ በኩል ሆነው በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን ፣ ፕሬዚዳንቱና ...
Read More »የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግዴታ ስለ አክራሪነት እና ሽብረተኝነት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በ2006 ዓም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፣ ሽብርተኝነት እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ትምህርት ለመስጠት የጀመረውን እቅድ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀምሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር። ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ በአዲስ ...
Read More »የስኳር እጥረቱ ለችግር ዳርጎናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢሳት እንደገለጹት በክልል ከተሞች ስኳርን በቀበሌዎች ለማከፋፈል የተደረገው ሙከራ በአላመስራቱ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ለልጆቻችን ሻሂ እና ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን ማዘጋጀት አልቻልንም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ቀደም ብሎ በቀበሌ በኪሎ 15 ብር ይሸጥ የነበረውን ስኳር፣ በ30 ብር ማግኘት እየተሳናቸው መምጣቱን ተናግረዋል። መንግስት ላለፉት 2 አመታት ዘይትና ስኳር በየቀበሌዎች ሲያከፋፍል መቆየቱ ይታወቃል።
Read More »ኢትዮጵያ በአለም ላይ በኢንተርኔት ስርጭት ከመጨረሻዎቹ ተርታ ተመደበች
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለማቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ማህበር ባወጣው መረጃ በአለም ካሉ አገራት ጊኒ ቢሳው፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማእከላዊ አፍሪካና ኒጀር የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በተቀራኒው ደቡብ ኮሪያ፣ ስዊድን፣ አይስላንድ፣ ዴን ማርክ፣ ፊንላንድ ፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድስ እንግሊዝና ሆንግ ኮንግ ከ አንድ እሰከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለግል ባለሀብቶች እንዲለቅ ግፊት ቢደረግበትም ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል። በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ ...
Read More »በአርባምንጭ የቴክኖሎጂ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።
መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምዘና ፈተና ጋር በተያያዘ በተማሪዎችና እና በዩኒቨርስቲው አስተዳደር መካከል በተፈጠረ ልዩነት ከ3 ሺ በላይ ተማሪዎች ዩኒቭረስቲውን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው በቤተክርስቲያናትና በሰዎች ቤት ተጠልለለው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ከእረፍት በተመለሱበት ማግስት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ የምዘና ፈተና ውሰዱ መባላቸውን ተቃውመው ተጨማሪ የጥናት ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ችግር መፈጥሩን ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲው ዲን በተማሪዎችላይ የተለያዩ ታፔላዎችን ...
Read More »