የስኳር እጥረቱ ለችግር ዳርጎናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

 መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢሳት እንደገለጹት በክልል ከተሞች ስኳርን በቀበሌዎች ለማከፋፈል የተደረገው ሙከራ  በአላመስራቱ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።

ለልጆቻችን ሻሂ እና ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን ማዘጋጀት አልቻልንም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ቀደም ብሎ በቀበሌ በኪሎ 15 ብር ይሸጥ የነበረውን ስኳር፣ በ30 ብር ማግኘት እየተሳናቸው መምጣቱን ተናግረዋል።

መንግስት  ላለፉት 2 አመታት ዘይትና ስኳር በየቀበሌዎች ሲያከፋፍል መቆየቱ ይታወቃል።