ደቡብ ሱዳን የአብየ ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ አለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበች

መስከረም (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል  እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል::

የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር ማለትም በጥቅምት ወር ይካሔዳል ቢልም ሰሜን ሱዳን ግን ከህዝበ ውሳኔ በፊት የፓለቲካ ውይይቶች እንዲቀድም ትፈልጋለች::

ከዚህ ጋር ተያይዞ በሰላም አስከባሪ ስም የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ሱዳን ነዋረዎች የኢትዮጵያን ሰራዊት ብቃት እየተጠራጠሩ ሲሆን በተለይ የዲንቃ የጐሳ አለቃ የሆነው ኩኦል ዴንግ ኩኦል የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለበት በመገደሉ ነዋሪው የኢትዮጵያ ሰራዊት በብቃት ህዝበ ውሳኔውን ያስፈፅማል ብለው እንደማይገምቱ በመናገር ላይ ናቸው::

አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት ስራቸውን ትተው ለስራ የሚሰጣቸውን ነዳጅና ቁሳቁስ በመሽጥ ላይ መሆናችውን የአካባቢው ነዋሪዎች በመናገር ላይ ሲሆኑ በአመራር ላይ ያሉትም የሰራዊቱ አዛዦች ባግባቡ ሰራዊቱን መምራት ሲገባቸው ስራቸውን ትተው በተባበሩት መንግስታት ሄልኮፕተር ከካርቱም እቃዎችን በማጓጓዝ በንግድ ላይ መሰማራታቸውን አብየ የሚገኙት ነዋረዎች በመናገር ላይ ይገኛሉ:::

በአብየ ያለው ሁኔታ ውጥረቱ እየጨመረ ሲሆን በድንገት በስሜን ሱዳንና በደቡብ ሱዳን መሃከል ጦርነት ይነሳል የሚል ስጋት እንዲያይል አድርጎታል። በትላንትናው እለት ያካባቢው ነዋረዎች ሪፈረደሙ ባስቸኳይ እነዲካሄድ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።