ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልዩ ሀይል እየተባለ በሚጠራው ታጣቂ ሚሊሺያ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያመለክት ዛጋቢ ፊልም በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ፣ የክልሉ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንቱን ቃለመጠይቅ በማድረግ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ አቀረበ። የክልሉ መንግስት በለቀቀው አዲስ ፊልም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አድናቆታቸውን የገለጹበት ክፍል የተካተተ ሲሆን፣ ይህም የፌደራሉ መንግስት ጉዳዩን አያውቀውም ...
Read More »በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ውጥረቱ ቀጥሎአል
ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፡ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ምሽት ላይ ጥይት ሲተኮስ ማምሸቱን የገለጹት አንዳንድ የተማሪዎች ቤተሰቦች፣ የተኩሱ ምክንያት ጩሀት የሚያሰሙ ተማሪዎችን ዝም ለማሰኘት ያለመ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በየክፍላቸው ሆነው ተቃውሞ እአሰሙ እንደሚገኙ የገለጹት ቤተሰቦች፣ አንዳንዶች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። ዩኒቨርስቲው አዲስ ...
Read More »አለማቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ
ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል። ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ...
Read More »የእስልምና እምነት ተከታዮች አረፋን በአል አከበሩ
ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ የሚከበረው የኢድ-አል አድሃ ( አረፋ) በአል ኢብራሂም ልጁን ለመስዋት ያቀረቡበትን እለት ለመዘከር ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው የበአል አከባበር ስነስርአት ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክስተቶች ታይተዋል። ዘወትር እንደሚደረገው የመጅሊስና አዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ንግግር አላደረጉም። ድምጻችን ይሰማ ትናንት ባወጣው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች መልእክቶችን ለማስተላለፍ ንግግር ማድረግ ከጀመሩ ህዝቡ በተቃውሞ እንዲያቋርጣቸው መመሪያ አስተላልፎ ...
Read More »በባህርዳር ከተማ የሚፈጸመው ሙስና ተባብሶ ቀጥሎአል።
ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ወኪሎች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በመስተዳድሩ ውስጥ የሚፈጸመውን ሙስና ማጋለቱን ተከትሎ መንግስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ከቦታቸው በማንሳት ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በማዛወር የህዝቡን ቅሬታ ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም፣ አሁንም በአስተዳደሩ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር በሚገኙት የከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፣ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ ሂደት እንዲሁም የልማታዊ ባለሀብት መሳብና ...
Read More »የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ወደ እንግሊዝ እስር ቤት ተላለፉ
ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለማቀፍ የወንጅል ፍርድ ቤት 50 አመታት የተፈረደባቸው ቻልረስ ቴለር በዛሬው እለት ለእንግሊዝ ፍርድ ቤት ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን፣ በሩዋንዳ እንዲታሰሩ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተድርጎባቸዋል። ፕሬዞዳንቱ በሴራሊዮን ለተፈጸመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት በሚል ዘሄግ የሚገኘው የወንጀል ፍርድ ቤት አምና የ50 አመታት እስር እንደፈረደባቸው ይታወቃል።
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በነገው ኢድ-አል አድሃ ላይ ተቃውሞ እንደሚያሰሙ ታወቀ
ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለወራት ተቋርጦ የነበረው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ነገ በመንግስት ባለስልጣናትና በመጅሊስ መሪዎች ንግግር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሎአል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ የመጅሊስ አመራሮች ንግግር የሚያደርጉ ከሆነ ንግግሩ እስኪቆም ድረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ተቃውሞው በመላ አገሪቱ እንደሚከናወን ድምጻችን ይሰማ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ፖሊስ ጸጥታ ለማስከበር ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ባወጣው ...
Read More »የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ
ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱን የትምህርት አመት ለመጀመር ምዝገባ ያጠናቀቁት ተማሪዎች ፣ ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ባነሱት ተቃውሞ የግቢው መስታውቶችና አንዳንድ አገልግሎት መስጪያ እቃዎች መሰባበራቸው ታውቋል፡፤ ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ግቢውን መቆጣጠሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የተቃውሞው መነሻ የዩነቨርስቲው ባለስልጣናት ከቤተከርስቲያን መልስ ነጠላ ለብሰው ወደ መመገቢያ ክፍል የገቡትን ተማሪዎች ፣ ነጠላ ለብሳችሁ መግባት አትችሉም በማለት በመከልከላቸው ነው ። ...
Read More »አቶ አዲሱ ለገሰ አራት ምክትሎች ተመደቡላቸው
ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሕአዴግ ካድሬዎችን ለማሰልጠን የተገነባውን የፖለቲካ ማሠልጠኛ ተቋም በሚኒስትር ማዕረግ ሲመሩ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተውጣጡ ምክትሎች ተሹመውላቸዋል፡ ፡ ከብአዴን አቶ ለገሰ ቱሉ፣ ከደሕዴን አቶ ወንድሙ ገዛኸኝ፣ ከሕወሓት አቶ ነጋ በርሄ ሲሆኑ፣ ከኦሕዴድ የተወከለው አመራር እስካሁን አለመታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል። ማሠልጠኛ ማዕከሉ በስድስት ዙሮች በርካታ ካድሬዎችን ያሰለጠነ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ ካድሬዎቹም ከሥልጠና በኋላ ...
Read More »ከሶስት ሚልየን በላይ ዜጎች ለወባ ወረርሽኝ ተጋልጠዋል
ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ወባ በሚያጠቃቸው ወረዳዎች ወረርሺኙ መከሰቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በገዳይነቱ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የሚይዘው የወባ በሺታ በአሁኑ ስዓት በአርሶ አደሩ ህይዎት ውስጥ ፈታኝ መሆኑን ከሁሉም ክልሎች ለፌድራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተላለፈው መረጃ ያመለክታል፡፡ በበሺታው ፈውስ አጥተናል የሚሉት ኗሪዎች ከገበያ እንደ ሸቀጥ እቃ የሚገዙዋቸው መዳህኒቶች የማዳን አቅም የላቸውም ይላሉ፡፡ በኢትዩጵያ የረጅ ድርጁቶች ...
Read More »