የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

ጥቅምት (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-አዲሱን የትምህርት አመት ለመጀመር ምዝገባ ያጠናቀቁት ተማሪዎች ፣ ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ባነሱት ተቃውሞ የግቢው መስታውቶችና አንዳንድ አገልግሎት መስጪያ እቃዎች መሰባበራቸው ታውቋል፡፤ ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ግቢውን መቆጣጠሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

የተቃውሞው መነሻ የዩነቨርስቲው ባለስልጣናት ከቤተከርስቲያን መልስ ነጠላ ለብሰው ወደ መመገቢያ ክፍል የገቡትን ተማሪዎች ፣ ነጠላ ለብሳችሁ መግባት አትችሉም በማለት በመከልከላቸው ነው ።

ተማሪዎቹ “መብታችንን ልትገፉን አትችሉም” በሚል ጩሀት ሲያሰሙ እንደነበረም ታውቋል።

በአሁኑ ጊዜ ሁኔታው መረጋጋቱን የገለጹት ተማሪዎች፣ አጋጣሚው ተማሪው በውስጡ አፍኖ ያዘውን ነገር በአደባባይ እንዲተነፍስ እድል ሰጥቶታል ብለዋል።