አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አውቶቡስ ተገልብጦ 6 ሰዎች ሞቱ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አውቶቡሱ 40 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደብረማርቆስ በጉዞ እያለ ነበር አባይ በረሃ ውስጥ የተገለበጠው። 6 ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ 11 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል:: ተሰፋሪዎቹ በደብረማርቆስ የሚካሄደውን የትምህርት ፊስቲቫል ለማክበር እየተጓዙ ነበር።

Read More »

በሱዳን በስድስት ጎረምሶች የተደፈረችው ወጣት ክስ ተመሰረተባት

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ ጉዳዩዋን ለማየት የተሰየመው  ፍርድ ቤት ቀጠሮው እንዲተላለፍ ወስኗል። ፖለስ በበኩሉ ኢትዮጵያዊቷ ወሲቡን የፈጸመችው እና በቪዲዮ እንዲቀረጽ የፈለገችው ተስማምታ ነው በማለት ዝሙት በመፈጸም ክስ  ሊመሰርት በሂደት ላይ ነው።  ፖሊስ ክሱን ለመመስረት የተነሳሳው  ወጣቷ እንደተደፈረች ወዲያውኑ ለፖሊስ ሪፖርት አላደረገችም በሚል ነው። ወጣቷ በበኩሉዋ ደፋሪዎቹ እንገድልሻለን በማለት ስላስፋሩዋት ወዲያዉኑ ሪፖርት ለማድረግ እንዳልቻለች ትገልጻለች። ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው  ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ ...

Read More »

የአሜሪካ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ መከላከያ እና ፖሊስ የሚሰጠው እርዳታ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወሰነ

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦሚኒበስ አፕሮፕሬሽን ቢል 2014  በድንጋጌው  ለኢትዮጵያ ወታደራዊና ፖሊስ ሃይሎች የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወስኗል። የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ካልጠበቀ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ካላከበረ፣ የሰዎችን የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና የሃይማኖት ነጻነትን ካላከበረ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ካለምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ስራቸውን እንዲሰሩ ካልተደረገ የአሜሪካ ኮንግረስ ድጋፍ አያደርግም ። እንዲሁም ...

Read More »

በተለያዩ ክልሎች ዜጎች በህገወጥ መንገድ መፈናቀላቸውን እየገለጹ ነው

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ በርካታ ነዋሪዎች ከ40 አመታት ላናነሰ ጊዜ የኖሩባቸውን ቤቶች እንዲለቁ መታዘዛቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ደግሞ ከ300 ያላነሱ ጉሊቶች ንብረታቸውን እየተቀሙ መደብሮቻቸው እንዲፈርስባቸው መደረጉ ታውቋል።ሰዎቹ ለረጅም ጊዜ ሲገለገሉበት የነበረውን ጉሊት እንዲያፈርሱ የተገደዱት ህገወጦች ናችሁ ተብለው ነው። ነዋሪዎች ...

Read More »

በ6 የሱዳን ወጣቶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በእስር ላይ እንደምትገኝ ታወቀ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሪያ እንድሪስ የተባለች ኢትዮጵያዊት ወጣት በ6 የሱዳን ወጣቶች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስትደፈር የሚያሳይ  ቪዲዮ ኢሳት  የደረሰው ሲሆን ፣ ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ልጂቷ መደፈሩዋን አምነው ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን ከፍተኛ ባለስልጣኖች መፍቀድ አለባቸው በሚል ዝርዝር ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ጥቅምት ወር አካባቢ ቤት ለመከራየት ...

Read More »

ሰመጉ በቁጫ ከ400 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን አንድ ሰው መገደሉን ገለጸ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው አንጋፋው የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ባወጣው 129 ልዩ መግለጫ  ” የሚለቀቁትን ሳይጨምር በሰላም በር ፖሊስ ጣቢያ 198 ሰዎች ፣በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት 212 ሰዎች ” መታሰራቸውን እና  ከሚደርሰው መንገላታት እና ጥቃት ለማምለጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሰደዳቸውን” ገልጿል። ቤቶች ...

Read More »

በኢትዮጵያ 6 ሚሊየን ሕዝብ ስር በሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ውስጥ ነው ተባለ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እ.ኤ.አ በ2013 ለሁለተኛው አጋማሽ ማለትም ከጁላይ እስከ ዲሴምበር የአስቸኩዋይ የእለት ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልገው 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሕዝብ የሚውል 162 ሺህ176 ሜትሪክ ቶን ምግብ ውስጥ ማሙዋላት የተቻለው 69 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን፣ 6 ሚሊየን ያህል ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ቤተሰቦች በሴፍትኔት መታቀፋቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ዛሬ ...

Read More »

የአሜሪካ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ ህዝብ የማያፈናቅልና የሰብአዊ መብት ጥሰት የማያባብስ መሆኑ እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ውሳኔ አሳለፈ።

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ የምርምር ተቋም ውሳኔውን ታሪካዊ ብሎታል። በኮንግረሱ የጸደቀው ኦምኒበስ አፕሮፕሬየሽንስ ቢል እየተባለ የሚጠራው ህግ (Omnibus Appropriations Bill) አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ ዜጎችን ለማፈናቀል እንደማይውል፣ ይህንንም ተከትሎ ሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱ ያረጋግጣል። በኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ነዋሪዎችን በማፈናቀል በሚደረገው ልማት ላይ የአሜሪካ እርዳታ ጥቅም ላይ እንዳይውል ህጉ ይከለክላል። የአሜሪካ እርዳታም  ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች 2 የኦብነግን መሪዎች አፍነው መውሰዳቸውን ግንባሩ ገለጸ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መረጃ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ኬንያ የሚገኙት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ሱሉብ አህመድና አሊ ሁሴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። መሪዎቹ የታፈኑት ናይሮቢ ውስጥ ሲሆን፣ ከመንግስት ጋር ለሚደረገው ሶስተኛ ዙር ውይይት ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ግንባሩ በመግለጫው ከዚህ ቀደምም የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የኦብነግ መሪዎችን ሲገድሉና ሲያፍኑ ...

Read More »